ለአርሶ አደሮችና ዓሳ ባለሙያዎች ስልጠና ተሰጠ

በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የማህበረሰብ አገልግሎት ፕሮግራም ለአርሶ አደሮችና ዓሳ ባለሙያዎች ስልጠና ተሰጠ፡፡

በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የማህበረሰብ አገልግሎት ፕሮግራም ከሲዳማ ክልል አስር ወረዳዎችና ከይርጋዓለም ከተማ አስተዳደር ለተውጣጡ ከ40 በላይ ለሚሆኑ አርሶ አደሮችና የዓሳ ባለሙያዎች ከግንቦት1-6/2014ዓ.ም ድረስ የንድፈ-ሃሳብ እና የተግባር ስልጠና ተሰጠ፡፡

በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የማህበረሰብ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ማርቆስ ፍስሃ እንደተናገሩት በዚህ ስልጠና በጥምር ግብርና የዓሳ እርባታ፣ የዓሳ አጠቃቀምና አመጋገብ ላይ በሰፊው የንድፈ-ሃሳብ ስልጠናዎች የተሰጡ ሲሆን ከዚህ በተጨማሪም ሰልጣኞችም የሰለጠኑትን በተግባር እንዲያዩት በዳሌ ወረዳ ይርጋለም ከተማ በአርሶ አደሮች ተዘጋጅቶ በኩሬ እየረባ ያለን የዓሳ እርባታን በተግባር እንዲያዩት እና ምርቱም ተጠምዶ ለምግብነት ሲውል የተግባር ልምድ እንዲቀስሙ የተደረገበት መሆኑን ገልፀዋል፡፡

በሀዋሳ ግብርና ማዕከል የዓሳ ተመራማሪ አቶ በረከት ሃጂ እንደገተናገሩት በዚህ ስልጠና የዓሳ ግብርና ፅንሰ ሃሳቦችን፣ የዓሳ መኖ አዘገጃጀትናአመጋገብ ፣ የጥምር ዓሳ ግብርና ፅንሰ ሃሳብንና አተገባበርን እንዲሁም የዓሳ ድህረ ምርት አያያዝና አመጋገብን በንድፈ ሃሳብ የተሰጠበትና በተግባርም ዓሳ እንዴት በኩሬ ተረብቶ፣ ተሰግሮና ተበልቶ ጥቅም ላይ እንደሚውል ያየንበት ነው ብለዋል፡፡

በስልጠናው ላይ ያገኘናቸው አርሶ አደሮች እንደተናገሩት በአሁኑ ሰዓት ሌሎች የእንስሳት ተዋፅኦ ውጤቶችን ከመጠቀም በዘለለ ዓሳ እርባታ ላይም ትኩረት በመስጠት አምርተን ለመመገብ፣ ለመሸጥና ኑሯችንን ለማሻሻል እንደምንችል ከስልጠናው በቂ የንድፈ-ሃሳብ እና የተግባር ስልጠና ያገኘን ሲሆን በቀጣይም በዚህ ዘርፍ ትኩረት ሰጥተን እንድንሰራ የሚመለከታቸው አካላት ድጋፍና ክትትል እንዲሁም የገብያ ትስስር እንዲፈጠር እንዲረዱን አደራ እንላለን ብለዋል፡፡

Contact Us

Office of External Relations & Communications 
Phone:  +251 46 220 5168
International Relations
Public Relations 

Touch Us

Registrar Contact 

Registrar Directorate 
Phone: 0462200229
Email: registrar@hu.edu.et