ተፈጥሯዊ ማዳበሪያ አመራረትና አጠቃቀም ላይ ለአርሶ አደሮች ስልጠና ተሰጠ

በመሬት ትል ተፈጥሯዊ ማዳበሪያ (ቨርሚኮምፖስት) አመራረትና አጠቃቀም ላይ ለአርሶ አደሮች ስልጠና ተሰጠ፡፡

በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የወንዶ ገነት ደንና ተፈጥሮ ሃብት ኮሌጅ የም/ቴ/ሽ/ ተባባሪ ዲን ፅ/ቤት በሲዳማ ክልል ዶሬ ባፈና ወረዳ ሳማ አጀርሳ ቀበሌ ለሚገኙ አርሶ አደሮች በመሬት ትል ተፈጥሯዊ ማዳበሪያ (ቨርሚኮምፖስት) አመራረትና አጠቃቀም ላይ በግንቦት 3 ቀን 2014 ዓ.ም ስልጠና ሰጥቷል፡፡

ዶ/ር ክብረስላሴ ዳንኤል የወንዶ ገነት ደንና ተፈጥሮ ሃብት ኮሌጅ የም/ቴ/ሽ/ ተባባሪ ዲን የዩኒቨርሲቲው ም/ቴ/ሽ/ም/ፕሬዝዳንት ፅ/ቤት ያወጣውን የምርምር ጥሪን ተከትሎ የኮሌጃችን ተመራማሪዎች ተወዳድረውና አሸንፈው ባገኙት የገንዘብ ድጋፍ በመሬት ትል ተፈጥሯዊ ማዳበሪያ (ቨርሚኮምፖስት) አመራረትና አጠቃቀም ላይ በርካታ ምርምሮችን እሰሩ የቆዩ ሲሆን ይሄንንም የምርምር ውጤት ለአካባቢው አርሶ አደሮች እያሰለጠኑ እና በተግባርም የሰሩትን ሰርቶ ማሳያ እያስጎበኙ ይገኛሉ ብለዋል፡፡

ዶ/ር ክብረስላሴ አክለውም አፈርን ለብዙ ዓመታት ከመጠቀማችን የተነሳ ለጎርፍ የመጋለጥ ዕድሉ እየሰፋ፣ የውሃ ስርገት መጠኑ እየቀነሰ፣ የካረቦን መጠን መቀነስ እና ማይክሮ ኦርኒዝሞችም መቀነስ በመታየታቸው አፈርን ለማከምና ጤናማ ለማድረግ፣ ለመጠበቅና ወደ ቀድሞ ሁኔታ ለመመለስ  እንዲሁም ተክሉ ምርታማ እንዲሆን የዚህ መሰሉ የተፈጥሮ ማዳበሪያ ጥቅሙ የጎላ መሆኑን ገልፀው ከዚህ በፊት የምንጠቀመው የአፈር ማዳበሪያ ኬሚካል በመሆኑ ለተክሉ እንጂ ለአፈሩ ጥቅም የሌለውና ማዳበሪያውን ለማግኘትም ከፍተኛ ወጪ  እንደሚያስፈልግ  ተናግረዋል፡፡

በምርምር የተገኘው ተፈጥሯዊ ማዳበሪያ (ቨርሚኮምፖስት) የሚዘጋጀውም በአካባቢው ከሚገኙ ተክሎች ተረፈ ምርቱን ትሎች እንዲመገቡት ከተደረገ በኃላ ከትሎቹ የሚወገደውን ከአፈር ጋር በማዋሃድ የሚገኝ በመሆኑ አርሶ አደሮቹ በቀላሉ በማዘጋጀት ጥቅም ላይ ማዋል እንደሚችሉ በስልጠናው ወቅት ያገኘነው መረጃ ያስረዳል፡፡

Contact Us

Office of External Relations & Communications 
Phone:  +251 46 220 5168
International Relations
Public Relations 

Touch Us

Registrar Contact 

Registrar Directorate 
Phone: 0462200229
Email: registrar@hu.edu.et