የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ እና አለም አቀፍ የአረንጓዴ ዕድገት ተቋም የጋራ መግባቢያ ሰነድ ተፈራረሙ

የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ እና አለም አቀፍ የአረንጓዴ ዕድገት ተቋም(GGGI) የጋራ መግባቢያ ሰነድ ተፈራረሙ፡፡

የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ መቀመጫውን ደቡብ ኮርያ ሲኦል ካደረገውና በኢትዮጵያም በአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር አረንጓዴ ኢኮኖሚ ልማትን ለመገንባት በሚያስችሉ ፕሮግራሞች ላይ እየሰራ ከሚገኘው  አለም አቀፍ የአረንጓዴ ዕድገት ተቋም( Global Green Growth Institute) ጋር በጋራ ለመስራት የሚያስችለውን  የመግባቢያ ሰነድ በሀዋሳ ሃይሌ ሪዞርት ተፈራረመ፡፡

ዶ/ር ገመዱ ዳሌ አለም አቀፍ የአረንጓዴ ዕድገት ተቋም(GGGI) በኢትዮጵያ ኃላፊ እንደተናገሩት ሀገራችንን በአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር አረንጓዴ ኢኮኖሚ ልማትን ለመገንባት የሚያስችሉ ትግበራዎች በአማራ፣ ኦሮሚያና ሲዳማ ክልሎች በተመረጡ እርጥበት አዘል ቦታዎች ላይ እየሰራች ያለችውን ስራዎች ለመደገፍ ተቋማችን በኢትዮጵያ አንጋፋ እና በምርምር ከተመረጡ ዩኒቨርሲቲ አንዱ ከሆነው የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ጋር በጋራ ለመስራት በዛሬው ዕለት ከስምምነት የደረስን ሲሆን ተቋማችን በተመረጡ የሲዳማና ኦሮሚያ ክልሎች ለሚተገበረው የምርምርና የአቅም ግንባታ ስራዎች ዩኒቨርሲቲውን በፋይናንስ፣ ተግባር ተኮር ምርምሮችን እና የቴክኒካል ድጋፎችን ያደርጋል፡፡

ዶ/ር አያኖ በራሶ የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት በበኩላቸው ዩኒቨርሲቲያችን በደን፣ ተፈጥሮ ሃብትና አየር ንብረት ለውጥ ላይ ለበርካታ ዓመታት ምርምሮችን፣ የማማከር ስራዎችን እና የአቅም ግንባታ ስራዎችን ለሀገራችን እና ለማህበረሰቡ እየሰራ ያለ የወንዶ ገነት ደንና ተፈጥሮ ሃብት ኮሌጅ እንዲሁም በተፋሰስና አፈር ጥበቃ እየሰራ ያለ የኢትዮጵያ ስምጥ ሸለቆ ጥናት ማዕከልን የያዘ በመሆኑ ከተቋሙ ጋር ለመስራት ተመራጭ ያደርገዋል ያሉ ሲሆን በስምምነቱ መሰረት በቀጣዮቹ ዓመታት በደን፣ አፈር ጥበቃ፣ በአየር ንብረት ለውጥና የአረንጓዴ ልማት እና ተያያዥ ጉዳዮች በርካታ መረጃዎችን በመሰብሰብ ምርምሮችን ከማድረግ በተጨማሪ የህብረተሰቡ የኑሮ እና ገቢ ሁኔታ የሚሻሻልበትን አማራጮችን በመፈተሸና በማምጣት የአቅም ግንባታ ስራዎችን የሚሰራ እና የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናዎችን ከተቋሙ ጋር በመተባበር የሚሰጥ ይሆናል ብለዋል፡፡

ስምምነቱም ከ3-5 ዓመታት እንደአስፈላጊነቱ ተፈፃሚ ሲሆን ይሄንንም ተግባራዊ ለማድረግ በሲዳማ እና ኦሮሚያ ክልሎች ከሚገኙ ጉዳዩ ከሚመለከታቸው አካላት ጋርም ተቀራርቦና ተቀናጅቶ እንደሚሰራ ለማወቅ ተችሏል፡፡

 

Contact Us

Office of External Relations & Communications 
Phone:  +251 46 220 5168
International Relations
Public Relations 

Touch Us

Registrar Contact 

Registrar Directorate 
Phone: 0462200229
Email: registrar@hu.edu.et