በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ዙሪያ ለጤና ባለሙያዎች ስልጠና መስጠት ተጀመረ

የሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ዙሪያ ከተለያዩ ክልሎች ለተውጣጡ የጤና ባለሙያዎች ስልጠና መስጠት ጀመረ፡፡

በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ኮቪድ-19 ወረርሽኝን በመደበኛው የሕክምና ስርዓት ውስጥ በማስገባት ታካሚዎችን እንዴት ማከምና ክትትል ማድረግ እንደሚቻል ከኦሮሚያ፣ ደቡብ እና ሲዳማ ክልሎች ለተውጣጡ 300 የሕክምና ባለሙያዎች በሶስት ዙር የሚጠናቀቅ ስልጠን ግንቦት 1 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ መስጠት ጀመሯል፡፡

ከኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስትቲዩት ኮቪድ-19 ናሚና አስተዳደር (Sampling Management) ዶ/ር ኤደን መዝገቡ  በስልጠናው ላይ ተገኝተው ኮቪድ-19 ወረርሽኝን ለመከላከልና ለመቆጣጠር እንደሀገር በርካታ ስራዎች እየተሰሩ ሲሆን አሁን ላይ ወረርሽኙን መቀነስ በመቻሉ እንደማንኛውም ተላላፊ በሽታዎች በመደበኛው  የሕክምና ስርዓት ውስጥ አገልግሎቱ እንዲሰጥ ተቀናጅቶ ለመስራትና የተጀመሩ ስራዎችን ለማስቀጠል እንዴት መሰራት አለበት የሚለውን ለሚመለከታቸው አካላት ሰልጠና በመስጠት ላይ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የምርምርና ቴክኖሎጂ ሽግግር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አለሙ ጣሚሶ (ረ/ፕ) በበኩላቸው ስልጠናው ከጤና ሚኒስቴር፣ ከኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስትቲዩት እና ከሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር በቅንጅት የሚሰጥ ሲሆን አለም አቀፍ፣ ሀገርአቀፍና አካባቢያዊ ጥናቶች እንደሚያሳዩት ወረርሽኙ አሁን ካለበት ሁኔታ አንፃር ብቻውን እንደወረርሽኝ ይዞ መቀጠል እንደማይቻል በመታመኑ እና ሕክምናው በሁሉም የሕክምና መስጫ ቦታዎች መሰጠትና ተደራሽ መሆን እንዳለበት በመታመኑ ወረርሽኙን እንዴት መከላከልና ማከም እንደሚቻል ለሚመለከታቸው አካላት ስልጠና እየተሰጠ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

በሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የተከታታይና የሙያ ክህሎት ማጎልበቻ ማዕከል አስተባባሪ ረቂቁ ፍቅሬ (ረ/ፕ) ስልጠናው ኮቪድ-19 ወረርሽኝን እንዴት መከላከል እንደሚቻል፣ መቆጣጠሪያና መመርመሪያ መንገዱን፣ በወረርሽኙ የተያዘን ሰው እንዴት ክትትልና ድጋፍ ማድረግ እንደሚቻል እና ከወረርሽኙ ጋር ተያይዞ የሚመጡ የስነ አእምሮና ጭንቀት በሽታዎችን እንዴት ማስተናገድ እንደሚቻል የሚረዳ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ከሶስቱም ክልልሎች ለተውጣጡ የጤና ጣቢያ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች፣ የጤና ፅ/ቤት ባለሙያዎች እና የጤና ኤክስቴንሽን ሱፐርቫይዘሮች እየተሰጠ ሲሆን የመጀመሪያው ዙር ከግንቦት1-3/2014ዓ.ም ድረስ ከተሰጠ በኃላ በቀጣይም ቀሪዎቹ  ሁለት ዙር ስልጠናዎችም በተያዘላቸው ጊዜ ተከታትለው እንደሚሰጡ ተናግረዋል፡፡

 

Contact Us

Office of External Relations & Communications 
Phone:  +251 46 220 5168
International Relations
Public Relations 

Touch Us

Registrar Contact 

Registrar Directorate 
Phone: 0462200229
Email: registrar@hu.edu.et