በሁለት የ3ኛ ድግሪ ፕሮግራሞች ላይ ግምገማ አካሄደ

የሕግና ገቨርናንስ ኮሌጅ በሁለት የ3ኛ ድግሪ ፕሮግራሞች ላይ ውጫዊ ግምገማ አካሄደ፡፡

በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ሕግና ገቨርናንስ ኮሌጅ የገቨርናንስ እና ልማት ጥናት ት/ቤት በሁለት የ3ኛ ድግሪ ፕሮግራሞች  ማለትም በልማት አስተዳደር (PhD in Development Management) እና በፖለቲካና አለም አቀፍ ግንኙነት    (PhD in Politics and International Relations) ላይ ውጫዊ ግምገማ በግንቦት 1 ቀን 2014 ዓ.ም አካሂዷል፡፡

ዶ/ር ደብረወርቅ ደበበ የሕግና ገቨርናንስ ኮሌጅ ዲን ኮሌጁ ላለፉት አስር ዓመታት በርካታ የሁለተኛ ድግሪ ፕሮግራሞችን ከፍቶ በማስተማርና በማስመረቅ በሀገራችን የሚታየውን የባለሙያዎች ዕጥረትና ክፍተት ለመሙላት ጥረት እያደረገ እና ምርምሮችን እየሰራ መሆኑን ገልፀው ባደረግነው የፌደራልና የክልሎች ተቋማት የፍላጎት ዳሰሳ ጥናት እና ከቀድሞ ምርቃኖቻችን በርካታ ጥያቄዎችና ፍላጎቶች መኖራቸውን መሰረት በማድረግ በሁለቱ ፕሮግራሞች ላይ ሰነዶች በአዘጋጅ ኮሚቴዎቹ ተዘጋጅተው ውስጣዊ ግምገማ ከዚህ ቀደም መደረጉን ተናግረዋል፡፡

ዶ/ር ደብረወርቅ አክለውም ከዚህ በፊት በውስጣዊ ግምገማው ወቅት የታዩ ክፍተቶችታርመውና በተሰጡት አስተያየቶች መሰረት ተስተካክለው በዛሬው ዕለት በዘርፉ በርካታ ዕውቀትና ልምድ ላላቸውና ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መጥተው ለሚገመግሙ ውጫዊ ገምጋሚዎች እንዲሁም ለዩኒቨርሲቲው ምሁራን ውጫዊ ግምገማ እንዲደረግበት የቀረበ ሲሆን በቀጣይም ከዚህ ግምገማ የሚሰጡትን ተገቢ አስተያየቶች በማረምና በማካተት ሰነዶቹ ተስተካክለውና ታርመው ተዘጋጅተው በዩኒቨርሲቲው እንዲፀድቁ ከተደረገ በኃላ በ2015ዓ.ም በእነዚህ ፕሮግራሞች ማስተማር እንደሚጀመር ተናግረው ከዚህ ጋር ተያይዞም ሌሎች ቅድመ ዝግጅቶች እንደሚደረጉ ገልፀዋል፡፡

በፕሮግራሙም ላይ ሁለቱም ሰነዶች በአዘጋጆቹ የቀረቡ ሲሆን የተጋበዙት ውጫዊ ገምጋሚዎች እና የዩኒቨርሲቲው ምሁራን መስተካከልና መታረም ያለባቸውን እንዲሁም በሰነዱ መካተት አለባቸው ያሉትን ነጥቦች አንስተው አስተያየት የሰጡ ሲሆን በተነሱት ነጥቦች ላይም ውይይት እና ከአቅራቢዎችም ግብረ መልስ ተሰጥቶባቸው ፕሮግራሙ ተጠናቋል፡፡

Contact Us

Office of External Relations & Communications 
Phone:  +251 46 220 5168
International Relations
Public Relations 

Touch Us

Registrar Contact 

Registrar Directorate 
Phone: 0462200229
Email: registrar@hu.edu.et