ፕ/ር ሃብታሙ ወንድሙ ሰላምን በሚመለከት ንግግር አደረጉ

ታዋቂው የሳይኮሎጂ ምሁር ፕ/ር ሃብታሙ ወንድሙ በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ተገኝተው ሰላምን በሚመለከት ንግግር አደረጉ፡፡

በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የማህበራዊ ሳይንስና ስነ-ሰብ ኮሌጅ ባዘጋጀው ፕሮግራም ላይ በመገኘት ከሀገራችን ወቅታዊ ሁኔታ ጋር ተያይዞ ብዝሃ ባህል ባለበት ማህበረሰብ ውስጥ ሰላምን እንዴት ማሳደግ እንደሚቻል እንዲሁም የምሁራኑ መልካም ዕድልና ተግዳሮቶች በሚል ርዕስ ዙሪያ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሚገኙት ታዋቂው የሳይኮሎጂተመራማሪና ምሁር ፕ/ር ሃብታሙ ወንድሙ በሚያዚያ 28/2014ዓ.ም ትምህርታዊ ንግግር አደረጉ፡፡

ፕ/ር ሃብታሙ ወንድሙ በንግግራቸው  ሰላም ምን ማለት እንደሆነ፣ ሰላምን እንዴት መገንባትና ማሳደግ እንደሚቻል፣ የሰላም መሰረታዊያን ምንድናቸው፣ ሰላምን በሚመለከት የሀገራችን ምሁራን ምን ሚና መጫወት እንዳለባቸው፣ ሀገራችን ያለችበትን ወቅታዊ ሁኔታ ከግምት ውስጥ በማስገባት ወዳሰብነው ልማት ለመምጣት ከምሁራኑ ምን ይጠበቃል የሚሉ ሃሳቦችን እና እንደ ኢትዮጵያ ብዝሃ ባህል ባለበት ሀገሮች ተቻችሎ፣ ተከባብሮ እና ፅንፈኝነትና አክራሪነትን በማስወገድ በሰላም ለመኖር የሚያስችሉ አለም አቀፍ ተሞክሮዎችን እና ተግዳሮቶችን በስፋት ያቀረቡ ሲሆን ተሳታፊዎችም በተነሳው ርዕስ ዙሪያ አለ ያሉትን ስጋቶችና መልካም አጋጣሚዎች በማንሳት ውይይትና ጠቃሚ ሃሳቦችን አንስተዋል፡፡

ዶ/ር ዳኜ ሽብሩ የማህበራዊ ሳይንስና ስነ-ሰብ ኮሌጅ ዲን በበኩላቸው ከዚህ ትምህርታዊ ንግግር ተሳታፊዎች ያገኙትን ትምህርትና ተሞክሮ ለተማሪዎቻቸው፣ ለወዳጅና ጓደኞቻቸው እንዲፅፉ፣ መሰል ምርምሮችን እንዲያበረክቱና እንዲያስተምሩ እንዲሁም ያሉትን ፕላት ፎርሞች ለመልካም አጋጣሚዎች እንዲጠቀሙበት የሚረዳ ሲሆን ሁሉም ባለድርሻ አካላትም በሰላም የመሰብሰብ፣ የመናገር፣ የመከባባር፣ የመወያየት የመሳሰሉ ባህሎችን ለማዳበር የበኩሉን ድርሻ መወጣት እንዳለበት በማሳሰብ የዚህ መሰሉን ፕሮግራምም በዩኒቨርሲቲ ደረጃ ወደፊት በማዘጋጀትና ምሁሩን በመጋበዝ ለዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ በሰፊው ተደራሽ እንደሚደረግ ተናግረዋል፡፡

Contact Us

Office of External Relations & Communications 
Phone:  +251 46 220 5168
International Relations
Public Relations 

Touch Us

Registrar Contact 

Registrar Directorate 
Phone: 0462200229
Email: registrar@hu.edu.et