በ9 ወራት ዕቅድ አፈፃፀም ላይ ግምገማ ተካሄደ

የአዋዳ ቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ በ9 ወራት ዕቅድ አፈፃፀም ላይ ግምገማ አካሄደ፡፡

በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የአዋዳ ቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ በ2014 በጀት ዓመት የዘጠኝ ወራት ዕቅድ አፈፃፀም ላይ ግምገማ እና ውይይት መጋቢት30 ቀን 2014 ዓ.ም አካሂዷል፡፡

በመድረኩ የኮሌጁ ሀብት ማመንጫ፣ ግዢና ንብረት አስተዳደር ቡድን እንዲሁም የአካውንቲንግና ፋይናንስ፣ ሎጀስቲክስና ሰፕላይ ቼይን ማኔጅመንት እና የማኔጅመንት ትምህርት ክፍሎች የዩኒቨርሲቲውን ስትራቴጂክ ዕቅድ መሰረት አድርገው በመማር ማስተማር፣ በምርምርና በማህበረሰብ አገልግሎት ኮሌጁ የተሰጠውን ተልዕኮ ለማሳካት ያቀዷቸውን እና ያከናወኗቸውን የዘጠኝ ወራት ዕቅድ አፈፃፀማቸውን በዝርዝር ያቀረቡ ሲሆን ያጋጠሙ ችግሮች፣ ተግዳሮቶችና የተወሰዱ መፍትሄዎችንም በማካተት ለመድረኩ አቅርበዋል፡፡

ዶ/ር ወገኔ ማርቆስ የአዋዳ ቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ ዲን በበጀት ዓመቱ እስካሁን ኮሌጁ ከፍተኛ አፈፃፀም በማስመዝገብ ላይ መሆኑን ገልፀው በዝርዝርም ቤተመፅሃፍት ዲጅታል መደረጋቸው፣ በመማሪያ ክፍሎች የነጭ ሰሌዳ መሟላታቸው፣ በሁለት የሶስተኛ ድግሪ ፕሮግራሞችና በአንድ የሁለተኛ ድግሪ ፕሮግራም የትምህርት ስርዓት ላይ ውጫው ግምገማ እንዲሁም በአንድ የሁለተኛ ድግሪ ፕሮግራም የትምህርት ስርዓት ላይ ውስጣዊ ግምገማ በማድረግ በቀጣይ ዓመት የድህረ-ምረቃ ፕሮግራማችንን ለማሳደግ መዘጋጀታችን፣ የንብረት አስተዳደር መተግበሪያ ጥቅም ላይ በማዋል አላስፈላጊ የሀብት ብክነቶችን ማስቀረት በመቻላችን፣ የመኪና ማቆሚያና ማጠቢያ ተሰርቶ አገልግሎት መጀመሩን እንዲሁም ገቢን በተመለከተ በዕረፍት ቀናት በምንሰጠው ትምህርት ካቀድነው በላይ ገቢ ሊገኝ ተችሏል ብለዋል፡፡

ዲኑ አክለውም የግዢ ስርዓት መጓተት፣ የገብያ አለመረጋጋትና ዋጋ መናር እንዲሁም የአስፈላጊ ግብዓቶች ከገብያ መጥፋት ያጋጠሙ ተግደሮቶች መሆናቸውን ገልፀው በቀሩት ወራቶችም ከምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ስራዎቻችን ጎን ለጎን  ተማሪዎችን ያለምንም እንከን አስተምሮ ለመጨረስ፣ የአይ ኤስ ቲ ማዕከል ለመክፈትና የግቢውን እግረኛ መንገድ ለማስዋብና ምቹ ለማድረግ ዝግጅት የጨረስን በመሆኑ የግቢው መምህራን እና ሰራተኞች የቀሩትን ተግባራት በጋራ ተናበን እና ተግተን እንድንሰራ አደራ እላለሁኝ ብለዋል፡፡

 

 

Contact Us

Office of External Relations & Communications 
Phone:  +251 46 220 5168
International Relations
Public Relations 

Touch Us

Registrar Contact 

Registrar Directorate 
Phone: 0462200229
Email: registrar@hu.edu.et