የቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት በ2014 ዓ.ም የ9 ወራት ዕቅድ አፈፃፀም ላይ ግምገማና ውይይት አካሄደ፡፡
በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት በ2014ዓ.ም የ9 ወራት ዕቅድ አፈፃፀም ላይ ግምገማና ውይይት መጋቢት 24 ቀን 2014 ዓ.ም ባካሄደበት ፕሮግራም ላይ የኢንስትቲውቱ ሳይንትፊክ ዳይይሬክተር ዶ/ር ኢንጅነር ፋሲካ ቤተ ተቋማት የተቋቋሙለትን ተልዕኮ ለማሳካት እንዲችሉ ከሚያደርጉ ተግባራት አንዱና ወሳኝ የሆነው ዕቅድ ማዘጋጀትና በዛም ዕቅድ መሰረት መመራት መቻል ሲሆን የእኛም የዛሬው ውይይትና ግምገማ መነሻ የዩኒቨርሲቲውን የ10 ዓመት ስትራቴጂክ ዕቅድ መነሻ በማድረግ በዓመቱ ለመስራት ካቀድናቸው ምንያህሉን በ9 ወራት ለማከናወን ቻልን፣ ያልተከናወኑ ምን ምን ተግባራት ይቀሩናል፣ በቀጣይስ ምን ማከናወን ይጠበቅብናል የሚሉትን እንዲሁም ያጋጠሙ ችግሮችንና ተግዳሮቶችንም መፍትሄ ለማበጀት በማሰብ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ዶ/ር ፋሲካ አክለውም የዛሬውን ውይይትና ግምገማ ለየት የሚያደርገው ሪፖርቱ ተዘጋጅቶ የሚቀርበው ከኢንስቲትዩት ደረጃ ዝቅ ብሎ በፋካሊቲና በቡድን መሪዎች ደረጃ በመሆኑ ጥሩ ተሞክሮ የሚፈጥርና የመድረክ አቀራረብ ልምድም የሚገኝበት ሲሆን የኢንስቲትዩውቱ መምህራንና ሰራተኞችም ዕቅድን የራስ በማድረግ የትምህርትን ጥራት ለማስጠበቅና ጥሩ ምሩቃንን ለማፍራት ሁሉም የየራሱን ድርሻ እንዲወጣ አደራ እያልኩኝ ዩኒቨርሲቲውም በግዢ ስርዓት መንጓተት ምክንያት ያልተሟሉልንን ግብዓቶች እንዲያሟላልን ለመጠየቅ እወዳለሁኝ ብለዋል፡፡
በፕሮግራሙም የ9 ወራት ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርቶች ቀርበውና ቀጣይ አቅጣጫዎችም ቀርበው ውይይቱ መጠናቀቁን ለማወቅ ተችሏል፡፡