የእጩ ዶ/ር ደሳለኝ ጃዊሶ የማሟያ ፅሁፍ የመጨረሻው ግምገማ ተካሄደ

በኢትዬጲያ እና ጀርመን ትብብር የፒ.ኤች.ዲ ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የቆዩት የእጩ ዶ/ር ደሳለኝ ጃዊሶ የማሟያ ፅሁፍ የመጨረሻው ግምገማ ተካሄደ።

መጋቢት 22 ቀን 2014 ዓ.ም በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት "Hydrometreological Trends and Impact of Land Use Dynamics on Stream Flow Generation in Case of Omo Gibe River Basin" በሚል ርዕስ በቀረበው የምርምር ጽሁፍ ላይ በተካሄደው በዚሁ ፕሮግራም ላይ የኢንስቲትዩቱ ሳይንቲፊክ ዳይሬክተር ዶ/ር ፋሲካ ቤቴ የማሟያ ጽሁፋቸውን ለሚያቀርቡት ዶ/ር ደሳለኝ ጃዊሳ እንኳን ደስ ያሎት ካሉ በኋላ በርካታ ባለሙያዎች በሌሉበት መሰል የምህንድስና ዘርፎች ላይ የሚካሄዱ ምርምሮች በተገቢው መንገድ ሊደገፉና ሊበረታቱ እንደሚገባ ገልጸዋል።

በቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት የድህረ ምረቃ ትምህርት ፕሮግራም አስተባባሪ የሆኑት ዶ/ር ማርቆስ ማቴዎስ በበኩላቸው ዶ/ር ደሳለኝ ጃዌሶ ላለፉት ሶስት አመታት በኢትዮጵያና በጀርመን ሀገር ሲከታተሉ የነበረውን የፒ.ኤች.ዲ ትምህርት በስኬት አጠናቀው ለዛሬው ቀን በመብቃታቸው የቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩቱ ትልቅ ደስታ እንደተሰማው ተናግረዋል። "Ethio-Germany Home Grown Sandwich Phd program" በተሰኘው የትምህርት እድል በቆዩባቸው የትምህርት ጊዜያት አማካሪ ሆነው ሲረዷቸው የነበሩት ከጀርመኑ ሮስቶክ ዩኒቨርሲቲ ዶ/ር በርናርድ እና ከአዲስ አበባ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ደግሞ ዶ/ር ብሩክ አባተ መሆናቸውን ገልጸው  እኚህ ልምድ ያካበቱ ባለሙያዎች ላደረጉት አስተዋጽኦ ምስጋና እንደሚገባቸው ገልጸዋል።

የውሀ አቅርቦትና አከባቢ ምህንድስና ትምህርት ክፍል ኃላፊዋ ወ/ሪት ትዝታ ግርማ ለዕጩ ዶክተሩ እንኳን ደስ ያሎት ብለው በሲቪል ምህንድስና የውሀ አቅርቦት ምህንድስና እስፔሻሊቲ ላይ እንደ ዩኒቨርሲቲም ሆነ እንደ ሀገር የሚታየውን የባለሙያ እጥረት በብዙ መልኩ የሚያሻሽል በመሆኑ የዛሬው ስኬት የተማሪው ብቻ ሳይሆን የሁሉም የዘርፉ ባለሙያዎች መሆኑን አስረድተዋል።

Contact Us

Office of External Relations & Communications 
Phone:  +251 46 220 5168
International Relations
Public Relations 

Touch Us

Registrar Contact 

Registrar Directorate 
Phone: 0462200229
Email: registrar@hu.edu.et