የገጠር መሬት አስተዳደር ሰልጣኞችን ተመረቁ

የወንዶ ገነት ደንና ተፈጥሮ ሀብት ኮሌጅ የገጠር መሬት አስተዳደር ሰልጣኞችን አሰልጥኖ አስመረቀ፡፡

በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የወንዶ ገነት ደንና ተፈጥሮ ሀብት ኮሌጅ የመሬት አስተዳደር እና ቅየሳ ትምህርት ክፍል ከግብርና ሚኒስቴር ጋር በመተባበር በደቡብ ክልል ከተለያዩ ቀበሌዎች ለተውጣጡ የገጠር ቀበሌ መሬት አስተዳደር ባለሙያዎች የአራተኝ ዙር የገጠር መሬት አስተዳደር ስልጠና ለ1 ወር  በመስጠት በመጋቢት 14/2014 ዓ.ም አስመረቀ፡፡

የመሬት አስተዳደር እና ቅየሳ ትምህርት ክፍል ኃላፊና የስልጠናው አስተባባሪ አቶ አስራት ጀርጌ ስልጠናውን አስመልክቶ ይህ ስልጠና ዋና ዓላማው  የገጠር መሬት አስተዳደር ስርዓትን ለማዘመን፣ ብሔራዊ የገጠር መሬት ስርዓትን ለመዘርጋትና አርሶ አደሩም ከመሬት ይዞታው ማግኘትና መጠቀም የሚገባውን መብትና ጥቅም እንዲያገኝና ገቢውን በማሳደግ የምግብ ዋስትናን እንዲያረጋግጥ ማስቻል እንዲሁም ከመሬት ይዞታ ጋር የሚነሱ ግጭቶችን ለመቀነስ ያለመ ነው ብለዋል፡፡

የወንዶ ገነት ደንና ተፈጥሮ ሀብት ኮሌጅ ዲን ዶ/ር ሞቱማ ቶሌራ በበኩላቸው ኮሌጁ ላለፉት በርካታ ዓመታት በደንና ተፈጥሮ ሀብት ዙሪያ ለሀገራችን በርካታ ባለሙያዎችን በማፍራት የበኩሉን እየተወጣ ሲሆን ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላትም ጋር በመተባበርም ለተለያዩ ባለሙያዎች የአቅም ግንባታ ስልጠናዎችን በመስጠት ላይ እንደሆነ ገልፀው ከግብርና ሚኒስቴር ጋር በመተባበር በደቡብ ክልል ለሚገኙ የቀበሌ መሬት አስተዳደር ባለሙያዎች የ1 ወር ስልጠና በተከታታይ ለ9 ዙሮች ለመስጠት የስምምነት ውል በገባነው መሰረት እስከአሁን 3 ዙር ያሰለጠንን ሲሆን በዛሬውም ዕለትም አራተኛውን ዙር አሰልጥነን ለማስመረቅ በቅተናል፡፡

የደቡብ ክልል የገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ኤጀንሲ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ኖህ ታደለ  ሰልጣኞችን ሲያስመርቁ ባስተላለፉት መልዕክት እንደገለፁት ለ1 ወር በኮሌጁ ያገኛችሁትን ዕውቀትና ክህሎት በመጠቀም የህብረተሰባችን ክፍል ለሆነው አርሶ አደር መፍትሄ የሚሆኑ የመሬት አስተዳደርን የሚመለከቱ ጉዳዮችን በተግባር ወደ መሬት በማውረድ ህዝባችሁን እንድታገለግሉ አደራ እያልኩኝ ለዚህ ቀን በመብቃታችሁ ተመራቂዎችም እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል፡፡

ፕሮግራሙም ስልጠናውን ለ 1ወር ለተከታተሉ 100 ሰልጣኞች ሰርተፍኬት ተሰጥቶ የተጠናቀቀ ሲሆን የአሁኑን ሰልጣኞችን ጨምሮ ኮሌጁ 400 ባለሙያዎችን ማስመረቁን እና በቀጣይም ስልጠናው መሰጠት እንደሚቀጥል ለማወቅ ተችሏል፡፡

Contact Us

Office of External Relations & Communications 
Phone:  +251 46 220 5168
International Relations
Public Relations 

Touch Us

Registrar Contact 

Registrar Directorate 
Phone: 0462200229
Email: registrar@hu.edu.et