ዓመታዊ የምርምር ግምገማ ጉባኤ ተካሄደ

የተፈጥሮና ኮምፒቴሽናል ሳይንስ ኮሌጅ ዓመታዊ የምርምር ግምገማ ጉባኤ አካሄደ፡፡

በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የተፈጥሮና ኮምፒቴሽናል ሳይንስ ኮሌጅ በኮሌጁ መምህራንና ተመራማሪዎች 6 ተሰርተው ባለቁ እና 5 እየተሰሩ ባሉ  በድምሩ 11 ምርምሮች ላይ ለመምከርና ለመወያየት ዓመታዊ የምርምር ግምገማ ጉባኤ መጋቢት 9 ቀን 2014 ዓ.ም አካሂዷል፡፡

በዩኒቨርሲቲው የተፈጥሮና ኮምፒቴሽናል ሳይንስ ኮሌጅ ዲን ዶ/ር ዘይቱ ጋሻው በጉባኤው መክፈቻ ላይ እንደተናገሩት ኮሌጃችን ከመማር ማስተማሩ ጎን ለጎን በ3 የሳይንስ ምርምር አቅጣጫዎች ላይ ማለትም በስነ-ህይወት፣ ፊዚካል እና ኮምፒቴሽናል ሳይንስ ላይ ትኩረት በመስጠት በርካታ ችግር ፈቺ ምርምሮችን እያካሄድን እና በማካሄድም ላይ ስንሆን በዛሬው ዕለትም የተሰሩት ጥናቶች ምን ላይ ያተኮሩ ናቸው፣ከታቀደላቸው በጀትና ጊዜ አንፃር  ምን ያክል ግባቸውን መተዋል፣ እንዴትና በምን አይነት መንገድ የማህበረሰቡን ችግር ፈትሸዋል እንዲሁም  ያላለቁትስ ከምን ደርሰዋል የሚለውን ለመገምገም፣ ለመወያየት እና ቀጣይ አቅጣጫዎችንም ለማስቀመጥ የታለመ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ዲኑ አክለውም ኮሌጃችን ባለድርሻ አካላትን ከተመራማሪዎቻችን ጋር በማቀናጀትና ማህበረሰቡ የሚፈልገውን ችግሮች መነሻ በማድረግ ከፌደራል ግብርና ሚኒስትር፣ ከደቡብና ሲዳማ ክልል ግብርና ቢሮች ጋር በዓሳ አመራረት ላይ፣ ከሲዳማ ክልል ማዕድንና ኢነርጂ ቢሮ ጋር በማዕድን ጥናት እንዲሁም ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በኢንዱስትሪዎች መስፋፋት ምክንያት ስለሚፈጠሩ ብክለቶችና ተያያዝ ጉዳዮች ላይ ጥናቶች እየተሰሩ መሆናቸውን ገልፀው የሚሰሩ ጥናት ውጤቶችም ለህብረተሰቡ እንዴት እንደሚተገበሩና ተደራሽ እንደሚሆኑ እንዲሁም ለሳይንሱ ማህበረሰብም በጆርናል ታትመው መውጣት እንዳለባቸው አቅጣጫዎችን በማስቀመጥና የአሰራር ስርዓቶችንም ዘርግተን እየተገበርን እንገኛለን ብለዋል፡፡

በፕሮግራሙም ላይ ጥናቶች በተመራማሪዎቹ ከቀረቡ በኃላ በተሳታፊዎች ውይይትና አስተያየት ተሰጥቶባቸው ፕሮግራሙ ተጠናቋል፡፡

 

 

 

Contact Us

Office of External Relations & Communications 
Phone:  +251 46 220 5168
International Relations
Public Relations 

Touch Us

Registrar Contact 

Registrar Directorate 
Phone: 0462200229
Email: registrar@hu.edu.et