ለሀዋሳ ከተማ ጡረተኛ አርሶ አደሮች ስልጠና ተሰጠ

ማህበረሰብ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ለሀዋሳ ከተማ ጡረተኛ አርሶ አደሮች ስልጠና ሰጠ፡፡

በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ምርምርና ቴክኖሎጂ ሽግግር ም/ፕ/ጽ/ቤት ስር የሚገኘው የማህበረሰብ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት በዘመናዊ ንብ እርባታ ዘሬ እና በከተማ የጓሮ አትክልት ልማት ላይ በሀዋሳ ከተማ ለሚገኙ ጡረተኛ አርሶ አደሮች ከየካቲት 24-26/2014 ዓ.ም ድረስ ስልጠና ሰጥቷል፡፡

የማህበረሰብ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ማርቆስ ፍስሃ  ዩኒቨርሲቲው ችግር ፈቺ ምርምሮችን በግብርና፣ በጤና፣ በትምህርት እንዲሁም በሌሎች ዘርፎችም በማድረግ እና የተለያዩ የቴክኖሎጂ ውጤቶችን ለተጠቃሚዎች የማሳወቅ፣ የማላመድ፣ ማሸጋገር እና የማስፋት ስራዎችን እየሰራ እንደሚገኝ አስታውሰው በዛሬው ዕለትም ከሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ግብርና መምሪያ ጋር በመተባበር በተጠቀሱት ርዕሶች ላይ በሀዋሳ ከተማ ለሚገኙ ጡረተኛ አርሶ አደሮች ያሉባቸውን የክህሎት ክፍተቶች በስልጠና ለመሙላትና ለመደገፍ እንዲሁም የጓሮ አትክልት ምርጥ ዘሮችን ለማከፋፈል እና በአይነት ከ20 የሚበልጡ የእርሻ መሳሪያዎች ማለትም አካፋ፣ ዶማ፣ ጋሪ፣ መኮትኮቻ፣ በራሱ መርጨት የሚችል ውሃ ማጠጫ እና የተወሰኑ ንብ ማነቢያ ቁሳቁሶችን ድጋፍ ለማድረግም ጭምር መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ሰልጣኞችም ባገኙት ስልጠናና ድጋፍ የክህሎት ክፍተታቸውን በመሙላት እና ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ ገቢያቸውን ያሻሽላሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ዳይሬክተሩ ተናግረዋል፡፡

 

Contact Us

Office of External Relations & Communications 
Phone:  +251 46 220 5168
International Relations
Public Relations 

Touch Us

Registrar Contact 

Registrar Directorate 
Phone: 0462200229
Email: registrar@hu.edu.et