የማህበራዊ ሳይንስና ስነ-ሰብ ኮሌጅ ዓመታዊ የምርምር አውደ-ርዕይ አዘጋጀ፡፡
በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ማህበራዊ ሳይንስና ስነ-ሰብ ኮሌጅ የምር/ቴ/ሽግግር ተባባሪ ዲን ጽ/ቤት ዓመታዊ የምርምር አውደ-ርዕይ የካቲት 25 ቀን 2014 ዓ.ም በዋናው ግቢ አዘጋጅቷል፡፡
በዩኒቨርሲቲው የማህበራዊ ሳይንስና ስነ-ሰብ ኮሌጅ የሆኑት ዶ/ር ዳኜ ሽብሩ በፕሮግራሙ መክፈቻ ላይ የምርምር አውደ-ርዕዩ ዓላማ በኮሌጁ መምህራንና ተመራማሪዎች በ2013 ዓ.ም የተሰሩ የጥናት ውጤቶች ቀርበው ውይይትና ግምገማ የሚደረግባቸው ሲሆን በ2014 ዓ.ም እየተሰሩ ያሉ ምርምሮች ከምን ደረሱ፣ ሂደቱ ምን ይመስላል፣ በኮሌጁ የሚሰሩ ምርምሮችና የማህበረሰብ አገልግሎት ስራዎች ምን ይመስላሉ የሚለውን እና የገጠሙ ተግዳሮቶችና ተሞክሮዎችም የሚፈተሹበትና የሚዳብሩበት መድረክ ከመሆኑም በተጨማሪ አዲስና ጀማሪ የሆኑ የኮሌጁ መምህራን በፕሮግራሙ በመሳተፍ ወደፊት ለሚሰሩት ጥናት ከነባር መምህራን ተሞክሮና ልምድ ይቀስማሉ ብለዋል፡፡
ዶ/ር ዳኜ በማስከተልም መምህራኖችም ችግር ፈቺ ምርምሮችና የማህበረሰብ አገልግሎት ስራዎች ላይ በመሳተፍ እንዲሁም የሰሯቸውን የምርምር ውጤቶችንም በማሳተም ለሳይንሱ ማህበረሰብ ተደራሽ ከማድረግም በተጨማሪ ለኮሌጁና ለዩኒቨርሲቲው በማቅረብ ተሰንደው እንዲደራጁ ማደረግ እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡
በማህበራዊ ሳይንስና ስነ-ሰብ ኮሌጅ የምርምርና ቴ/ ሽግግር ተባባሪ ዲን ዶ/ር መለሰ ማዳ በአዲሱ ፖሊሲ አቅጣጫ መሰረት መምህራኖቻችን የምርምር ስራዎችን መስራትና ማሳተም እንዲሁም በማህበረሰብ አገልግሎት ስራዎች ላይም መሳተፍ ግድ መሆኑን በመረዳት ችግሮችን ተቋቁመውና ለሀገር መስራትን አላማቸው በማድረግ ያላቸውን እውቀት እንዲያበረክቱ እና የመንግስት አስፈፃሚ አካሎችም እንዲሁ ከተመራማሪዎች ጋር ተቀራርቦ በመስራት ችግር ፈቺ የምርምር ውጤቶች ተግባራዊ እንዲሆኑ የበኩላቸውን እንወጡ ጥሪያቸውን አቅርበዋል፡፡