ሕፃናትን ለማሰተማር ከኤስ ኦ ኤስ የሕፃናት መንደር ጋር የፕሮጄክት ውል ስምምነት ተፈራረመ

ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ ምክንያቶች ለችግር የተጋለጡ ሕፃናትን ለማሰተማር ከኤስ ኦ ኤስ የሕፃናት መንደር ጋር የፕሮጄክት ውል ስምምነት ተፈራረመ።

በዩኒቨርሲቲው የምርምርና ቴክኖሎጅ ሽግግር ምክትል ፕሬዝዳንት ዶ/ር ታፈሰ ማቲዎስ በፕሮግረሙ ላይ በደረጉት የመክፈቻ ንግግር ዩኒቨርሲቲው ልዩ ትኩረት ሰጥቶ ከሚሠራባቸው ስራዎች መካከል የትምህርት ጥራትና አግባብነትን ማጎልበት ስራዎች ዋነኛው ሥሆን  ለዚህም ይረዳ ዘንድ በትምህርት ዘርፍ ያሉ ችግሮችን በጥናት በመለየት የመፍተሄ ሃሳቦችን ለሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ማሳወቅና ትምህርት ቤቶችን በግብአት መደገፍ እንዲሁም ለመምህራንና ለትምህርት ቤት አመራር የአቅም ግንባታ ስልጠናዎችን የመስጠት ተግባራት በስፋት እየተካሄዱ መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡

ለትምህርት ጥራት ዋነኛ ከሆኑ እንቅፋቶች መካከል ከሕፃናት ማቆያ ፕሮግራም ጀምሮ በትምህርት ላይ የሚሠሩ ሥራዎች ልዩ ትኩረት እንዲምያስፈልግ በጥናት መረጋገጡን ጠቆሙት ዶ/ር ታፈሰ ማቲዎስ የበለጠ ውጤታማ ለማድረግ በአከባቢው በትምህርት ላይ ከሚሠሩ መንግስታዊ ያልሆኑ ዓለም አቀፍ ተቋማት ጋር በትብብር መስራት አስፈላግ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

በዚህም መሠረት በሕፃናት መሠረታዊ ትምህርት ላይ በጋራ ለመስራት በዘርፉ ከፍተኛ ልምድ ካከበተው ኤስ ኦ ኤስ የሕፃናት መንደር ጋር ለሚቀጥሉት 3 ዓመታት ሥራ ላይ የሚውል የ7.2 ሚሊዮን ብር የፕሮጄክት ውል ስምምነት ተፈራሪሟል፡፡

በተመደበው በጀት በሀዋሳ ከተማ አስተዳደር በጨፌ ኮቴጃዌሳ ትምህርት ቤት ለሚማሩ ተማሪዎች፤ የተማሪ ወላጆችንና ትምህርት ቤቱን የመደገፍ ስራ የሚሠራ ሥሆን በተመሳሳይ መልኩ ላለፉት 3 ዓመታት በተመደበው የ5.6 ሚሊየን ብር በጀት ዩኒቨርሲቲው ከኤስ ኦ ኤስ የሕፃናት መንደር ጋር ያከናወናቸው ሥራዎች ተገምግመው ውጤታማ መሆናቸው በዘርፉ ባለሙያዎች ተገምግሞ ማለፉን ከዶክቴር ታፈሰ ገለጻ ለመረዳት ተችሏል፡፡

የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዶ/ር አያኖ በራሶ በዚሁ ጊዜ እንዳብራሩት የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ሀገራዊ ለውጡን ተከትሎ በሀገር አቀፍ ደረጃ ወደ ምርምር ዩኒቨርሲቲነት ከሚያድጉ የከፍተና ትምህርት ተቋማት አንዱ ሆኖ መመረጡንና ዩኒቨርሲቲው ካለው ሰለጠነ የሰው ሀይል፤ የምርምር መሠረተ ልማትና የምርምር ሕትመቶችና ውጤቶች አንፃር  በግብርናና በስነ ሕይወት፤ ጤና፤ በፈዚክስ፤ ሳይንስና ቴክኖሎጅ፤ ምህንዲስና እንዲሁም በማኀበራዊ ሳይንስ ዘርፎች ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እንዲሠራ በመንግስት አቅጣጫ መቀመጡን ጠቁመዋል፡፡

በዚሁ መነሻ የ10 ዓመት ስትራቴጂክ አቅድ አዘጋጅቶ በመስራት ላይ ያለ ሲሆን በ2023 ዓም በምስራቅ አፍሪካ ከምገኙ አስር ቀዳሚ ዩኒቨርሲቲዎች መካከል አንዱ የመሆን ራዕይ ይዞ በቁርጠኝነት በመስራት ላይ የሚገኝ መሆኑንና ለዚህም ቀጣይነት ያለውን የትምህርት ጥራት ለማረጋገጥ የሚያስችሉ መሠረታዊ ስራዎችን በስፋት ለማከናወን በታዳግ ሕፃናት ላይ መስራት አማራጭ የሌለው መፍትሔ መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡

በፕሮግራሙ ላይ የታደሙት ተማሪዎች በዚሁ ጊዜ በሰጡት አስተያየት ከትምህርት ቤት ዩኒፎርም ጀምሮ በሚደረግላቸው የትምህርት መርጃ ቁሳቁሶች ሳይቸገሩ ለመማር መቻላቸውንና በተረጅ ተማሪዎች መካከል በሚደረገው የውጤት ፉክክርና ሽልማት የበለጠ ለማጥናት እያነሳሳቸው መሆኑን አስረድተዋል፡፡  

Contact Us

Office of External Relations & Communications 
Phone:  +251 46 220 5168
International Relations
Public Relations 

Touch Us

Registrar Contact 

Registrar Directorate 
Phone: 0462200229
Email: registrar@hu.edu.et