የተፈጥሮና ቀመር ሳይንስ ኮሌጅ የ2014 ዓ.ም የግማሽ ዓመት የስራ አፈፃፀም ግምገማ አካሄደ

በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የተፈጥሮና ቀመር ሳይንስ ኮሌጅ የ2014 ዓ.ም የግማሽ ዓመት የስራ አፈፃፀም ግምገማ እና ምክክር በታህሳስ 27/2014ዓ.ም አካሂዷል፡፡

የተፈጥሮና ቀመር ሳይንስ ኮሌጅ ዲን የሆኑት ዶ/ር ዘይቱ ጋሻው በመክፈቻው ላይ እንደተናገሩት ይህ መድረክ  የኮሌጁን የስድስት ወር ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት አዘጋጅተን ለዩኒቨርሲቲው ከማቅረባችን በፊት በኮሌጃችን የሚገኙ ትምህርት ክፍሎች፣ ፋካሊቲዎች እና ማዕከሎች እንደዩኒቨርሲቲው በተሰጡን 9 ግቦች ላይ ከመማር ማስተማር፣ ከምርምርና ቴ/ሽግግር እና ማህበረሰብ አገልግሎት አንጻር የተሰሩ ስራዎች  አፈፃፀምን በዝርዝር በማየት ክፍተቶቻችን ላይም በመመካከር በቀጣይ የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ የመፍትሄ አቅጣጫዎችን እንድናስቀምጥ ይረዳናል ብለዋል፡፡

በዕለቱም የፋካሊቲ ዲኖች፣ የትምህርት ክፍልና የማዕከል ኃላፊዎች የስድስት ወር አፈፃፀም ሪፖርታቸውንያቀረቡ ሲሆን በቀረቡትም ሰነዶች ላይ ግምገማና ውይይት በማድረግ ፕሮግራሙ ተጠናቋል፡፡ 

 

Contact Us

Office of External Relations & Communications 
Phone:  +251 46 220 5168
International Relations
Public Relations 

Touch Us

Registrar Contact 

Registrar Directorate 
Phone: 0462200229
Email: registrar@hu.edu.et