የወንዶ ገነት ደንና ተፈጥሮ ሀብት ኮሌጅ በሁለት ስርዓተ- ትምህርቶች ላይ ውስጣዊ ግምገማ አካሄደ

የወንዶ ገነት ደንና ተፈጥሮ ሀብት ኮሌጅ በሁለት ስርዓተ- ትምህርቶች  ላይ ውስጣዊ ግምገማ አካሄደ፡፡

በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የወንዶ ገነት ደንና ተፈጥሮ ሀብት ኮሌጅ በዘላቂ የአፈር አያያዝ ለመጀመሪያ ግዜ በሶስተኛ ድግሪ እንዲሁም በተፋሰስ አያያዝ ደግሞ ክለሳ በማድረግ  በሁለተኛ ድግሪ ተማሪዎችን ተቀብሎ ለማስተማር  በሁለቱ ስርዓተ- ትምህርቶች  ዝግጅት ላይ ውስጣዊ ግምገማ በታህሳስ23/2014ዓ.ም አካሄደ፡፡

ረዳት ፕሮፌሰር ያደታ ተሾመ በኮሌጁ የአፈር ሃብትና የተፋሰስ አያያዝ ትምህርት ክፍል ኃላፊ እንደተናገሩት ሀገራችን በግብርናው ላይ ጥገኛ የሆነች በመሆኑ እና በግብርናውም ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ እየደረሰ ያለውን የመሬት መሸርሸርና የአፈር መታጠብ ለማስቀረት እንዲሁም የመሬትና የአፈር አጠቃቀማችንን እና የውሃ ሀብት አጠቃቀማችንንና አያያዛችንን ለማሻሻል በዘርፉ እውቀትና ብቃት ያለው የተማረ የሰው ሃይል አስፈላጊ በመሆኑ ፕሮግራሞቹን ኮሌጁ ለመክፈት አስቦ የስርዓተ-ትምህርቶቹን ዝግጅት አጠናቆ ውስጣዊ ግምገማ እያካሄደ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

በዕለቱም የሁለቱም ስርዓተ- ትምህርት  አዘጋጆች ሰነዶቹን ያቀረቡ ሲሆን ከተሳታፊዎች በተሰጡት አስተያየቶችና ምክሮች በመነሳት መስተካከያዎች ተደርጎበት ለቀጣይ ውጫዊ ግምገማ እንደሚቀርብ ከአዘጋጆቹ ለማወቅ ተችሏል፡፡

Contact Us

Office of External Relations & Communications 
Phone:  +251 46 220 5168
International Relations
Public Relations 

Touch Us

Registrar Contact 

Registrar Directorate 
Phone: 0462200229
Email: registrar@hu.edu.et