ሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ አዲስ የሕዝብ ግንኙነት ባለሙያዎች የአቅም ግንባታ ስልጠና ተሰጠ

የሀዋሳ ኒቨርሲቲ የሕዝብ ግንኙነትና ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ለሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ አዲስ የሕዝብ ግንኙነት ባለሙያዎች የአቅም ግንባታ ስልጠና ሰጠ።

የዋናው ግቢ የሕዝብ ግንኙነትና ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ከ12-13/04/14 ዓ.ም ስልጠናውን ያዘጋጀው ከሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ቺፍ ኤክሴኪዩቲቭ ዳይሬክተር ጽ/ቤት ጋር በመተባበር ሲሆን የስልጠናው ዓላማ አዲሱን የኮሌጁን ሕዝብ ግንኙነት ስታፍ በዜና አጠነቃቀር፣ በሪፖርት አጻጻፍና በመረጃ አሰናነድ ላይ አቅም ማጎልበቻ ድጋፍ ማድረግ ነው፡፡

የዳይሬክቶሬቱ ዳይሬክተር ረ/ፕ ማቴዎስ ወ/ጊዮርጊስ በሕዝብ ግንኙነት አንኳር ርዕሰ-ጉዳዮች  ያንድን ተቋም እይታ ከማጎልበት አንጻር ትኩረት ተሰጥቶ መሠራት ባሉባቸው ሀሳቦች ላይ ጠቅለል ያሉ ጉዳዮችን በማንሳት ያሰለጠኑ ሲሆን በዜና አጻጻፍ ስርዓትና በጋዜጠኝነት የሙያ ዘርፍ መታወቅ ያለባቸው ጉዳዮች ላይ የዳይሬክቶሬቱ የሚዲያና ህትመት ባለሙያ አቶ ስለሺ ነጋሽ ማሰልጠናቸው ታውቋል፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ የዳይሬክቶሬቱ የኦዲዮቪዥዋል ባለሙያ የሆኑት አቶ ሀይሌ በይ ጥራት ያላቸውን ፎቶግራፎች በማንሳት ረገድ በካሜራ አጠቃቀምና ለተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎችና ለህትመት ጥራታቸውን የጠበቁ ፎቶግራፎች በተለያየ መጠን በመጠቀም አግባብነት ላይ ግንዛቤ የሚያስጨብጥ ተግባር ተኮር ስልጠና መስጠታቸው ተዘግቧል፡፡

በመጨረሻም የኮሌጁ የቺፍ ኤክሴኪዩቲቭ ዳይሬክተር ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ አበባየሁ ቱናሻ ለአዲሱ የቅርንጫፍ ሕዝብ ግንኙነት ክፍል ባለሙያዎች የተደረገው ድጋፍ ወሳኝ መሆኑን በመጠቆም ባለሙያዎቹን በተከታታይነት የማብቃት ሀላፊነትን በዋናው ግቢ ዳይሬክቶሬቱ ላይ ከመጣላችን ባሻገር በኮሌጃችን የሚከናወኑ በርካታ ተግባራት መረጃ በዩኒቨርሲቲ ደረጃ በጊዜና በጥራት ደርሶ እንዲሰራጭ አብረን መሥራት እንዳለብን እረዳለሁ ብለዋል፡፡ ሰልጣኞቹም ከጠበቁት በላይ በቂ ስልጠና ማግኘታቸውን ገልጸው የተደረገላቸው ድጋፍ ለድንበር የለሽ ሰፊው ሕዝብ አገልግሎት እየሰጠ ያለውን የተቋማቸውን እይታ ለማጎልበት የሚያስችላቸው መሆኑን ተናግረዋል፡፡   

 

Contact Us

Office of External Relations & Communications 
Phone:  +251 46 220 5168
International Relations
Public Relations 

Touch Us

Registrar Contact 

Registrar Directorate 
Phone: 0462200229
Email: registrar@hu.edu.et