የሕግና ገቨርናንስ ኮሌጅ የግማሽ ዓመት ክንውን ሪፖርት ግምገማና የአቅም ግንባታ ስልጠና ሰጠ

የሕግና ገቨርናንስ ኮሌጅ የግማሽ ዓመት ክንውን ሪፖርት ግምገማና የአቅም ግንባታ ስልጠና ሰጠ፡፡

በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የሕግና ገቨርናንስ ኮሌጅ የ2014ዓ.ም ግማሽ ዓመት ክንውን ሪፖርት ግምገማና ለኮሌጁ ኃላፊዎችና አስፈፃሚዎች በዕቅድና ሪፖርት አዘገጃጀት ላይ በታህሳስ21/2014ዓ.ም በሻሸመኔ ከተማ የአቅም ግንባታ ስልጠና ተሰጠ፡፡

በዩኒቨርሲቲው የሕግና ገቨርናንስ ኮሌጅ የሆኑት ዶ/ር ደብረወርቅ ደበበ በመክፈቻ ንግግራቸው የፕሮግራሙ ዓላማ የግማሽ ዓመት ክንውን ሪፖርት የሚቀርብበት፣ ከቀረበው ሰነድም በመነሳት ግምገማና አስተያየት የምንሰጥበት እንዲሁም ደግሞ በዕቅድና ሪፖርት አዘገጃጀት ላይ ያሉብንን ክፍተቶች ለመሙላትና ብዥታዎችን ለማጥራት የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና የሚሰጥበት መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የኮሌጁ ዲን አክለውም ዓመቱ በኮቪድ ወረርሽኝ ምክንያትና ከግዢ ስርዓት መዘግየት ጋር ተያይዞ ሲንከባለል የመጣ በርካታ ተዳራራቢ ስራዎችን የሰራንበት ቢሆንም ይህ መድረክ ጥንካሬያችን እና ጉድለቶቻችን ላይ በመምከርና በመገምገም በስራ ሂደቶቻችን ላይ የሚኖረንን መስተጋብሮች በመለየትና እርምት በማድረግ በቀጣይ አፈፃፀማችን ላይ የላቀ ውጤት ለማምጣት ታቅዶ የተዘጋጀ በመሆኑ ተሳታፊዎች በንቁ እንዲሳተፉ አሳስበዋል፡፡

በዕለቱም በኮሌጁ የሚገኙ ት/ቤቶችና ት/ክፍል ኃላፊዎች እንዲሁም የአካዳሚክ ጉዳዮችና የም/ቴ/ ሽግግር ተ/ዲኖች በኩል ሪፖርቶች ቀርበው በጠንካራና ደካማ ጎኖቻቸው ላይ ውይይት የተካሄደ ሲሆን በቀጣይም በዩኒቨርሲቲው የዕቅድና ተቋማዊ ለውጥ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሙልጌታ ቡርቃ በዕቅድና ሪፖርት አዘገጃጀት ላይ የግንዛቤ ማስፊያ ሙያዊ ማብራሪያ ተስጥቶና ውይይት ተካሂዶ ፕሮግራሙ ተጠናቋል፡፡

Contact Us

Office of External Relations & Communications 
Phone:  +251 46 220 5168
International Relations
Public Relations 

Touch Us

Registrar Contact 

Registrar Directorate 
Phone: 0462200229
Email: registrar@hu.edu.et