የማህበራዊና ሳይንስና ስነ-ሰብ ኮሌጅ የ2014 ዓ.ም ስድስት ወራት ዕቅድ አፈፃፀም ላይ ግምገማ አካሄደ

በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የማህበራዊና ሳይንስና ስነ-ሰብ ኮሌጅ የ2014 ዓ.ም የመጀመሪያው ስድስት ወራት ዕቅድ አፈፃፀም ላይ ግምገማና ውይይት በታህሳስ21/2014ዓ.ም በሻሸመኔ ከተማ አካሄደ፡፡

ዶ/ር ዳኜ ሽብሩ የማህበራዊና ሳይንስና ስነ-ሰብ ኮሌጅ ዲን በመክፈቻ ንግግራቸው እንደገለጹት ኮሌጁ የመማር ማስተማሩን፣ የምርምርና የማህበረሰብ አገልግሎት ስራዎቹን አጠናክሮ እየሰራ ሲሆን በቀጣይም በተሻለና በላቀ ሁኔታ አፈፃፀማችንን ለማሳደግ እንዲረዳን የትያትሪካል አርት፣ የካውንስሊንግ(የማማከር) እና የጂኦግራፊ ት/ክፍሎች  ቢሮዎችን እንዲሁም የጆርናሊዝም፣ አንትሮፖሎጂና ቻይንኛ  ቤተ- ሙከራዎችን በተሻለ ሁኔታ የማደረጀት ስራዎች እየተሰሩ እና በኮሌጁ የሚሰሩ ምርምሮችም በጆርናሎች ላይ እየታተሙና ተደራሽ እየሆኑ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

የኮሌጁ ዲን አክለውም በኮሌጃችን በርካታ ስራዎች ቢሰሩም በአንዳንድ ት/ቤቶችና ክፍሎች በአግባቡ በየጊዜው ተመዝግበው ባለመያዛቸው ጊዜውን  እና ጥራቱን የጠበቀ ሪፖርት ለማዘጋጀት እና ለመሰነድ ክፍተቶች እየታዩ መሆናቸውን ጠቅሰው በዚህ መድረክ ግን ሪፖርቶች ቀርበው ከመወያየት በዘለለ በዕቅድ  እና ሪፖርት አዘገጃጀት ላይ ሙያዊ አስተያየታቸውን እና ድጋፋቸውን ሊሰጡን የዩኒቨርሲቲው ዕቅድና ተቋማዊ ለውጥ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተርና ባለሙያ በመሃላችን ስለሚገኙ ተሳታፊዎችም በቀረበው ሪፖርት ላይ በመወያየትና የሚሰጡንን ሙያዊ አስተያየቶችም  እንደግብዓት በመውሰድ በቀጣይ የተሻሉ ሰነዶች ማደራጀትን መሰነድ ይኖርብናል ብለዋል፡፡

በዕለቱም በኮሌጁ የሚገኙ ት/ቤቶችና ት/ክፍል ኃላፊዎች እንዲሁም የአካዳሚክ ጉዳዮችና የም/ቴ/ ሽግግር ተ/ዲኖች በኩል ሪፖርቶች ቀርበው በጠንካራና ደካማ ጎኖቻቸው ላይ ውይይት እንዲሁም በሪፖርት አዘገጃጀት ላይ ሙያዊ አስተያየት ተሰጥቶባቸው ፕሮግራሙ መጠናቀቁን ለማወቅ ተችሏል፡፡

Contact Us

Office of External Relations & Communications 
Phone:  +251 46 220 5168
International Relations
Public Relations 

Touch Us

Registrar Contact 

Registrar Directorate 
Phone: 0462200229
Email: registrar@hu.edu.et