በህግ ትምህርት ቤትና በህግ ተማሪዎች ማሕበር አዘጋጅነት የሃምሳለ ፍርድ ቤት ዉድድር ተካሄደ።
የህግ ትምህርት ክፍል ኃላፊ የሆኑት አቶ በሃይሉ እሸቱ የዉድድሩን የመክፈቻ ንግግር ባደረጉበት ወቅት የተዘጋጀዉ ፕሮግራም ተማሪዎች ስለ ፍርድ ቤት ሂደት የበለጠ እንዲያዉቁ ዉድድሩ የህግ ትምህርት ቤተ-ሙከራ አንደሆነና ዉድድሩ ለወደፊት የህግ ተማሪዎች ስለ ሃምሳለ ፍርድ አሰጣጥ ሂደት የተሻለ ግንዛቤ ከወዲሁ ጨብጠዉ እንዲሄዱ ከማስቻል ባለፈ ብቁና ተወዳዳሪ በማድረግ ረገድ ከፍተኛ እንደሆነ ገልፀዋል፡፡
በህግ ትምህርት ክፍል ተማሪና የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የሕግ ተማሪዎች ማሕበር ፕሬዝዳንት የሆነችው ተማሪ መድሃኒት ተሻለ ዉድድሩን አስመልክታ ይህ በህግ ተማሪዎች መካከል የሚደረገዉ የሀምሳለ ፍርድ ቤት ዉድድር በተለያዩ መድረኮች ላይ በሕግ ትምህርት ክፍል ዙሪያ የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲን ወክለዉ በመሳተፍ የዩኒቨርሲቲዉን ስም ለማስጠራት ከወዲሁ አንዲዘጋጁ ይረዳል ብለዋል፡፡ ለወደፊትም አሸናፊ ተማሪዎች ከተለዩ በዉኃላ ከወላይታ ሶዶ፣ ከአርባምንጭና ከዲላ ዩኒቨርሲቲ የሕግ ተማሪዎች ጋር ዉድድር እንደሚደረግ ተናግራለች፡፡
በመጨረሻም የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የህግና ገቨርናንስ ኮሌጅ ዲን ዶ/ር ደብረወርቅ ደበበ የፕሮግራሙን የመዝጊያ ንግግር ሲያደርጉ በተወዳዳሪ ተማሪዎቸ እጅግ እንደተደሰቱና ወደፊትም ዩኒቨርሲቲዉን በሕግ ትምህርት መስክ ከፍተኛ ውጤት በማምጣት እንደሚያስጠሩ ባለሙሉ እምነት እንደሆኑ ተናግረዋል፡፡