"አረንጏዴነት ለጋራ ልማት" በሚል መሪ ቃል የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የአረንጏዴ ልማትና የፅዳት ዘመቻ አካሄደ፡፡
በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ጽ/ቤት ኃላፊ የሆኑት አቶ አየለ አደቶ የዘመቻዉን መክፈቻ ንግግር ባደረጉበት ወቅት አንደተናገሩት የዩኒቨርሲቲዉ ማሕበረሰብ በቅድሚያ የቆሻሻ ብቻ ሳይሆን የቆሸሸ አስተሳሰብን አስወግዶ ለሌሎችም ተምሳሌት መሆን እንደሚገባ ጠቅሰዉ ተማሪዎች በዘመቻዉ ወቅትም ሆነ ሁልጊዜ ዶርማቸዉን| አከባቢያቸዉን እንዲሁም ትምህርታቸዉን ጨርሰዉ ወደ አከባቢያቸዉ ሲመለሱ የመጡበትን አከባቢ በማፅዳትና በማልማት ሀገራዊ ንፅህናን ማስጠበቅ ይገባቸዋል ብለዋል፡፡
በየዓመቱ የሚካሄደዉ ይህ የአከባቢ ልማትና ፅዳት ዘመቻ በተለያዩ ምክንያቶች በተለይም በመላዉ ዓለም ላይ የተከሰተዉ የኮቪድ-19 ወረርሺኝና የአየር ንብረት ለዉጥ ምክንያት ዘመቻዉ ሳይካሄድ እስካሁን እንደቆየ የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የሴቶች ህጻናት ወጣቶችና ኤች.አይ.ቪ.ኤድስ ጉዳዮች ዳይሬክተር ወ/ሮ ምህረት ገነነ ተናግረዋል፡፡ አክለዉም ዘመቻዉ የተካሄደዉ UNFPA እና TOGETHER FOR BETTER FUTURE (OSSHD) ከተባሉ አጋር ድርጅቶች ጋር በጋራ በመሆን እንደሆነ ጠቅሰዉ ከዚህ በፊት ዘመቻዉን ለማካሄድ የገጠሙትን ችግሮች በመቅረፍና የክበቡን አባላትን በማሳደግ እንዲሁም በማጠናከር ለወደፊቱ የተሻለ ለመስራት አቅደናል ብለዋል፡፡
የልማትና የፅዳት ዘመቻዉን የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የሴቶች ህጻናት ወጣቶችና ኦች.አይ.ቪ.ኤድስ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት የክበባት መሪዎችንና ተማሪዎች በትብብር በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ዋናዉ ግቢ የአከባቢ ጥበቃና እንክብካቤ እንዲሁም የጽዳት ዘመቻዉን በጋራ አካሂደዋል፡፡