የተራቆተ መሬትን መልሶ በማልማት ለተደራጁ ስራ-አጥ ወጣቶች ተጠቃሚ እንዲሆኑ ርክክብ ተደረገ

የተራቆተ መሬትን መልሶ በማልማት ለተደራጁ  ስራ-አጥ ወጣቶች ተጠቃሚ እንዲሆኑ ርክክብ ተደረገ፡፡

የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ምርምርና ቴክኖሎጂ /ሽ/ም/ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት ስር በኤዶ ድንጋይ ማውጫ መልሶ ማልማት ፕሮጀክት በኩል  በወንዶ ገነት ወረዳ ኤዶ ቀበሌተፈጥሮን መሰረት ባደረገ መልኩ ተሰርቶ የለማውን መሬት በቀበሌው ለተደራጁ  ስራ-አጥ ወጣቶች ለማስተላለፍና ስለተፈጥሮ ሀብት ዘለቄታዊ አጠቃቀም ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ  መድረክ በወንዶ ገነት ባሻ ከተማ በታህሳስ12/2014ዓ.ም ተካሄደ፡፡

ዶ/ር ሙሉጌታ ዳዲ የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪና የፕሮጀክቱ አስተባባሪ እንደተናገሩት ከዚህ በፊት በቦርቻና  በአዲሱ አየር መንገድ አካባቢ በተፈጥሮ፣ ሰው ሰራሽና ደለል እንዲሁም የተለያዩ ችግሮች ያሉበትን መሬት ሳይንሳዊና ተፈጥሮአዊ በመሆነ በኢኮ ሃይድሮሎጂ መንገድ በማከም  ለልማት፣ ከምግብ ዋስትና ጋር የማስተሳሰር፣ ለወጣቶች የስራ ዕድል መፍጠር፣ ጎርፍን መቆጣጠር፣ ደለልን የመያዝ እና ለሌሎች ተመራማሪዎች ሰርቶ ማሳያ የማድረግ ስራዎች ሰርተው ውጤታማ  መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡ ዶ/ር ሙሉጌታ አክለውም ይህም በኤዶ ቀበሌ የሚገኘው የተራቆተ ድንጋይ ማውጫ መሬት ከዚህ በፊት በአካባቢው መንገድ ሲሰራ ቦታው ላይ ያለው አፈር ተወስዶ መልሶ ሳይለማ በመቅረቱና ቀሪውም አፈር በጎርፍ ተጠርጎ ተወስዶ የነበረ ሲሆን ከ2010ዓ.ም ጀምሮ በተደረገው ጥረት መልሶ እንዲያገግምና  አፈር እንዲይዝ ተደርጎ ተክሎችም እየበቀሉበት ይገኛል ብለዋል፡፡

አቶ ዳዊት ሌዳሞ የወንዶ ገነት ወረዳ አስተዳደር ኃላፊ እንደገለጹት ይህ ቦታ ፕሮጀክቱ ባደረገው ምርምርና ክትትል በመልማቱ በጎርፍ ምክንያት የሚፈናቀሉ አርሶ አደሮች እንዳይፈናቀሉ መደረጉን፣ ቦታው ለልማት አመቺ በመሆኑ ወጣቶችም ተደራጅተው ቦታውን በመጠቀም ኑሯቸውን እንዲያሻሽሉበት በመደረጉ ለተደረገው ድጋፍ አመስግነው የሚረከቡትም ወጣቶች በባለቤትነት በመጠቀም ለተተኪው ትውልድ እንዲያቆዩ አሳስበዋል፡፡

 

 

 

Contact Us

Office of External Relations & Communications 
Phone:  +251 46 220 5168
International Relations
Public Relations 

Touch Us

Registrar Contact 

Registrar Directorate 
Phone: 0462200229
Email: registrar@hu.edu.et