የዓለም ፀረ- ሙስና ቀን በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ ዝግጅቶች ተከበረ

የዓለም ፀረ- ሙስና ቀን በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ ዝግጅቶች ተከበረ።

በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ18ኛ በሀገራችን ለ17ኛ ጊዜ “በሥነ-ምግባር የታነፀ አመራር ከሙስና ለፀዳች ኢትዮጵያ” በሚል መሪ ቃል በተካሄደው የአከባበር ሥነ-ሥርዓት ላይ የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት አማካሪ አቶ ግርማ ጩሉቄ ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር ዩኒቨርሲቲው በስሩ በሚገኙት 7 ካምፓሶች ከ43 ሺ በላይ ተማሪዎችን ከሁሉም የሀገሪቷ አከባቢዎች ተቀብሎ በማስተማር ላይ የሚገኝ መሆኑንና ከቀለም ትምህርት በተጨማሪ በሥነ-ምግባር የታነፀ፤ ከሙስና የፀዳ፤ ለሀገር ተቀርቋር ዜጋ ለመቅረጽ በየካምፓሶች የፀረ-ሙስና ማስተባበሪያ ክፍል እንዲኖር መደረጉን ገልጸዋል፡፡ በዩኒቨርሲቲው ትምህርታቸውን ቀስመው የሚወጡ ተማሪዎች በሥነ-ምግባር የታነጹና ሀገር ወዳድ እንዲሆኑ ለማድረግ የሚደረገው ሁሉ አቀፍ ጥረቶች ተጠናክረው የሚቀጥሉ መሆናቸውንም አስረድተዋል፡፡

በበዓሉ ላይ ከየካምፓሶቹ በውጤታቸው በተመረጡ ተማሪዎች መካከል  የጥያቄና መልስ ውድድር ፤ ልዩ ተስጥኦ ባላቸው ተማሪዎች አዝናኝ የሆኑ ተውነታዊ ጭውውቶችና ግጥሞች ከመቅረባቸውም በላይ ለጀግናው የሀገር መከላከያ ሠራዊት የደም ልገሳ ፕሮግራም ተካሄዷል፡፡   

በመጨረሻም የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ሥነ ምግባርና ፀረ-ሙስና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ከበደ ኩማ ባደረጉት የማጠቃለያ ንግግር ፕሮግራሙ እንዲሳካ ላደረጉትና በዕለቱ ደማቸውን ለሀገር መከላከያ ሠራዊት ለለገሱት የዩኒቨርሲቲው ማኀበረሰብ  አመስግነዋል፡፡ 

በዩኒቨርሲቲው የሴነት መሰብሰቢያ አዳራሽ በተካሄደው ፕሮግራም ከሁሉም ካምፓሶች የተጋበዙ መምህራንና የአስተዳደር ሠራተኞች እንዲሁም የዋናው ግቢ ተማሪዎች ተሳትፈዋል፡፡     

Contact Us

Office of External Relations & Communications 
Phone:  +251 46 220 5168
International Relations
Public Relations 

Touch Us

Registrar Contact 

Registrar Directorate 
Phone: 0462200229
Email: registrar@hu.edu.et