የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ለጀግናው ለአፋር ወንድም ህዝብ ከ2 ሚሊዮን ብር በላይ የዓይነት ድጋፍ አደረገ።
ታህሳስ 01 ቀን 2014 ዓ.ም የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ለጀግናው ለአፋር ወንድም ህዝብ በአፋር ዋና ከተማ ሰመራ ዩኒቨርሲቲ በመገኘት ከ2 ሚሊዮን ብር በላይ የአልባሳት፣ የምግብ ግብአትና ቁሳቁስ ድጋፍ አድርጓል። የአፋር ህዝብ የሀገር ሉአላዊነትን ለማስጠበቂ የከፈለው አስደናቂ መስዋዕትነትና ያደረገው ተጋድሎ እጅግ የሚመሰገን መሆኑን በማስታወስ ኢትዮጵያን እንደ ሀገር ይዞ ለማስቀጠል በጋራ በመደጋገፍ ሁሉም የበኩሉን አስተዋጽኦ ማበርከት እንዳለበት ተገልፆአል። በተጨማሪም ከሰመራ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንትና ማኔጅመንት ጋር በተደረገው ውይይት ከሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ጋር ከወንድማማች ግንኙነት ባሻገር የስትራቴጂካዊ ግንኙነት ላይ መሰረት በማድረግ ለቀጣይ መሥራት እንደሚገባ መስማማት ላይ ተደርሷል።
ድል ለኢትዮጵያ!
ድል ለመላው ጥቁር ህዝቦች!
ውድቀት ለወራሪዎችና ፀረ-ኢትዮጵያ ሃይሎች