የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የ2014ዓ.ም የአንደኛ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ላይ ውይይት አደረገ

የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የ2014ዓ.ም የአንደኛ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ላይ ውይይት አደረገ።

የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ በስሩ የሚገኙትን ኮሌጆችና እና ኢንስቲትዩቶቹ በ2014ዓ.ም የአንደኛ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ላይ በዕቅድና ፕላን ዳይሬክቶሬት በኩል እንዲቀርብ ተደርጎ በታዩት ክፍተቶች እና ቀጣይ ስራዎች ላይ ውይይትና ምክክር አካሄደ፡፡
የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶ/ር አያኖ በራሶ በመክፈቻ ንግግራቸው እንደተናገሩት የዚህ ሩብ ዓመት አፈጻጸም ሪፖርትና ውይይት በተለያዩ ሀገራዊና ውስጣዊ ምክንያቶች ሳይቀርብ ቢቀርም በዛሬው ዕለት እንደዩኒቨርሲቲ የሩብ ዓመት አፈጻጸሙን የምንገመግም ሲሆን እንደሚታወቀው ዩኒቨርሲቲ በርካታ ስራዎችን በመማር ማስተማር፣ በምርምርና ቴክኖሎጂ ሽግግር እና ማህበረሰብ አገልግሎት ላይ እንዲሁም ሀገራዊ ጥሪን ጭምር በመቀበል የበኩሉን እየተወጣ ቢሆንም ክፍተቶች ስለሚኖሩ ከዚህ በመነሳት በቀጣይ ስራዎቻችንን ለመከወን መወሰድ ስለሚገባቸው ማስተካኬዎችና እርምቶች ላይ እንመክራለን ብለዋል፡፡ዶ/ር አያኖ አክለውም በየኮሌጆች እና ኢንስቲትዩቶች ላይም በሪፖርትና ዕቅድ አዘገጃጀት ዙሪያም በተያያዘ መልኩ ለአመራሮች አቅጣጫ የሚሰጥበት መድረክ ይሆናል ብለዋል፡፡

በመድረኩም የፕላን እና ዕቅድ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሩብ ዓመቱን አጠቃላይ አፈጻጸም ለዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ እና መካከለኛ አመራሮች ቀረቡ ሲሆን ተሳታፊዎችም በቀረበው ሰነድ ላይ ተወያይተው ቀጣይ አቅጣጫዎችን በማስቀመጥ ብሮግራሙ ተጠናቋል፡፡

Contact Us

Office of External Relations & Communications 
Phone:  +251 46 220 5168
International Relations
Public Relations 

Touch Us

Registrar Contact 

Registrar Directorate 
Phone: 0462200229
Email: registrar@hu.edu.et