የቴክኖሎጂ ሽግግርና የዩኒቨርሲቲ-ኢንዱስትሪ ትስስር ዳይሬክቶሬት የምክክር መድረክ አካሄደ

የቴክኖሎጂ ሽግግርና የዩኒቨርሲቲ-ኢንዱስትሪ ትስስር ዳይሬክቶሬት የምክክር መድረክ አካሄደ።

በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የቴክኖሎጂ ሽግግርና የዩኒቨርሲቲ- ኢንዱስትሪ ትስስር ዳይሬክቶሬት ከፌደራል ምግብ፣ መጠጥና ፋርማሲዩቲካል ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት ጋራ በመተባበር በባለፈው ዓመት የዩኒቨርሲቲ- ኢንዱስትሪ ትስስር  ዕቅድ አፈጻጸምና የ2014ዓ.ም ዕቅድ ላይ፣ በምግብ ደህንነት ፍተሻ እና በስርዓተ- ፆታ አካቶ መስራት ላይ በተከናወኑ ተሞክሮዎች ዙሪያ ከህዳር 23 -24/2014ዓ.ም ድረስ በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የምክክር መድረክ አካሄደ፡፡

ዶ/ር ታፈሰ ማቲዎስ የምርምርና ቴ/ ሽግግር ም/ ፕሬዝዳንት በመክፈቻ ንግግራቸው እንደገለፁት ዩኒቨርሲቲዎች በኢንዱስትሪዎች ውስጥ የሚሰራን የሰለጠነ የሰው ኃይል የሚያፈሩ ብቻ ሳይሆኑ የኢንዱስትሪዎችን ችግር የሚፈቱ አዳዲስ እውቀቶችንና ቴክኖሎጂዎችን የሚያፈልቁ ተቋማት ሲሆኑ በሌላ በኩል ኢንዱስትሪዎች ደግሞ ለሀገራዊ ሁለንትናዊ ዕድገት የሚያስፈልጉ ምርቶችን የሚያመርቱና አገልግሎቶችን የሚሰጡ በመሆናቸው ዩኒቨርሲቲዎች የሚፈጠረው ቴክኖሎጂ፣ የሚሰራው ምርምር፣ የሚፈራው የሰለጠነ የሰው ኃይል የኢንዱስትሪዎችን ፍላጎት መሰረት ያደረገና ችግር የሚፈታ መሆን አለበት ብለዋል፡፡

ዶ/ር ታፈሰ አክለውም የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የቴክኖሎጂ ሽግግርና የዩኒቨርሲቲ- ኢንዱስትሪ ትስስር ዳይሬክቶሬትም ባለፉት አምስት ዓመታት ከሀዋሳ  ኢንዱስትሪ ፓርክ፣ ከይርጋለም የተቀናጀ  ግብርና ኢንዱስትሪ ፓርክ፣ ከኢትዮጵያ ተፋሰስ ባለስልጣን  እንዲሁም ከሲዳማናደቡብ ክልሎች የተለያዩ ቢሮዎች ጋር ትስስሮችን ፈጥሮ የተለያዩ ስራዎችን እየሰራ እና በርካታ የፈጠራ ቴክኖሎጂዎችንም ወደ ኢንዱስትሪዎች እንዲሸጋገሩ ተደርጓል ብለዋል፡፡

የፌደራል ምግብ፣ መጠጥና ፋርማሲዩቲካል ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት ም/ ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ በላይነሽ ኩምሳ  በምክክር መድረኩ የሚመለከታቸው አካላት  ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች፣ ቴክኒክና ሙያዎች፣ ኢንዱስትሪዎች እና ፋብሪካዎች  ተገኝተው  በተነሱት ርዕሰ-ጉዳዮች ላይ በአግባቡ ኃሳባቸውንና የመፍትሄ አቅጣጫዎች ላይም በመወያየታቸው የውይይት መድረኩ የተሳካ እንደነበር እንዲሁም ደግሞ  በቀጣይ ጊዚያቶችም  የተገኙ ቴክኖሎጂዎችና ተሞክዎችም ተደራሽ እንዲሆኑ በጋራ በርትቶ መሰራት እንዳለበት ገልፀው የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የቴክኖሎጂ ሽግግርና የዩኒቨርሲቲ- ኢንዱስትሪ ትስስር ዳይሬክቶሬትም የምክክር መድረኩ እንዲሳካ ላደረገው አስተዋፅኦ ምስጋና ይገባዋል ብለዋል፡፡

 

                                     

Contact Us

Office of External Relations & Communications 
Phone:  +251 46 220 5168
International Relations
Public Relations 

Touch Us

Registrar Contact 

Registrar Directorate 
Phone: 0462200229
Email: registrar@hu.edu.et