የስነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ዳይሬክቶሬት ለተማሪዎች የጥያቄና መልስ ዉድድር አካሄደ

የስነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ዳይሬክቶሬት ለተማሪዎች የጥያቄና መልስ ዉድድር አካሄደ።

በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የስነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ዳይሬክቶሬት “በስነ-ምግባር የታነፀ ጠንካራ ትዉልድ እንገነባለን” በሚል መሪ ቃል የጥያቄና መልስ ዉድድር ሕዳር 20 ቀን 2014 ዓ.ም በዋና ግቢ አዘጋጅቷል፡፡

የእንኳን ደህና መጣችሁ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት ሀላፊ የሆኑት አቶ አየለ አዳቶ በስነ-ምግባር የታነፀ ጠንካራ ትዉልድ ለሀገራችን ያስፈልጋታል ያሉ ሲሆን በአሁን ሰዓት የገጠማትን ችግር በድል እንደምትወጣ ገልፀዉ የመክፈቻ ንግግራቸዉን አጠቃለዋል።

በዕለቱም ለተወዳዳሪ ተማሪዎች የተለያዩ ጥያቄዎች ቀርበው ዉድድሩ ተደርጎ የመዝጊያ ፕሮግራም ተከናውኗል። በዉድድሩም ከፍተኛ ዉጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች ዩኒቨርሲቲዉን ወክለው በሌሎች ውድድሮች እንደሚሳተፋ ተገልጿል።

 

Contact Us

Office of External Relations & Communications 
Phone:  +251 46 220 5168
International Relations
Public Relations 

Touch Us

Registrar Contact 

Registrar Directorate 
Phone: 0462200229
Email: registrar@hu.edu.et