በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የግል ጥንስስ አጠቃላይ ቤተ-መዘክር ተከፈተ

በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የግል ጥንስስ አጠቃላይ ቤተ-መዘክር ተከፈተ።

የቤተመዘክሩ መስራች እና ባለቤት የሆኑት መምህር ይርጋወሰን የማርያምወርቅ እንደገለጹት ቤተ-መዘክሩን ከ1975 ዓ.ም ጀምሮ ለተማሪዎቻቸው መማሪያ መርጃ እንዲሆን በማሰብ ከሰበሰቧቸው የታሪክ መጽሃፍት፣ ስዕሎች፣ ባህላዊና ታሪካዊ ዕቃዎች በመነሳት ሲሆን ለመጀመሪያ ጊዜም በ1987 ዓ.ም በቤታቸው ቤተ-መዘክሩን (ሙዚዬም) በመክፈት ለህዝብ ግልጋሎት እንዲውል ማድረጋቸውን ተናግረዋል፡፡

መምህር ይርጋወሰን አክለውም ቤተመዘክሩ በውስጡ ዕድሜያቸው  ከመቶ ዓመት በላይ የሆኑ የታሪክ መጽሃፍት፣ ስዕሎች፣ ባህላዊና ታሪካዊ ዕቃዎችን የያዘ በመሆኑ የዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች እና ተመራማሪዎች ሀገራችን ከዚህ ቀደም የነበረችበትን ሁኔታ ለማወቅና ለመመራመር ስለሚረዳቸው ቤተመዘክሩን እንዲጎበኙ እና የበኩላቸውን ሙያዊ እገዛ እንዲያደርጉ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል፡፡

በመጨረሻም ቤተመዘክሩን ለማደራጀት ከዚህ በፊት የፌደራል ቅርስና ጥበቃ ባለስልጣን፣ የደቡብና የሲዳማ ክልል ቱሪዝም ቢሮዎች እንዲሁም የሀዋሳ ከተማ ባህልና ቱሪዝም መምሪያ ሙያዊ ድጋፍ ያደረገልኝ ሲሆን በአሁኑ ሰዓትም የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ቅርሶቹን የማሳይበት ቦታ ስለሰጠኝ ልባዊ ምስጋና አቀርባለሁኝ ብለዋል፡፡

ቪዲዮው ከደቡብ ቴ/ሬ/ድርጅት ከተወሰደው ሊንክ ይከታተሉ፣  https://www.youtube.com/watch?v=TiOfkLU04B4

 

 

Contact Us

Office of External Relations & Communications 
Phone:  +251 46 220 5168
International Relations
Public Relations 

Touch Us

Registrar Contact 

Registrar Directorate 
Phone: 0462200229
Email: registrar@hu.edu.et