በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የነጭ ሪቫን ቀንን አስመልክቶ የፀረ-ፆታዊ ጥቃትን ለመከላከል ንቅናቄ ተጀመረ

በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የነጭ ሪቫን ቀንን አስመልክቶ የፀረ-ፆታዊ ጥቃትን ለመከላከል ንቅናቄ ተጀመረ።

የሴቶች፣ ህጻናት፣ ወጣቶችና ኤች.አይ.ቪ ኤድስ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት የፀረ-ፆታዊ ጥቃትን አስመልክቶ በዓለም ለ30ኛ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ13ኛ ጊዜ የሚከበረውን የነጭ ሪቫን ቀንን አስመልክቶ “ ሰላም ይስፈን በሴቶች እና ህፃናት ላይ የሚደርስ ጥቃት ይቁም” በሚል መሪ ቃል ንቅናቄ ተጀመረ፡፡

ወ/ሮ ምህረት ገነነ የሴቶች፣ ህጻናት፣ ወጣቶችና ኤች.አይ.ቪ ኤድስ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር እንደተናገሩት እንደሚታወቀው በሴቶችና ህጻናት ላይ በአለምና ሀገር አቀፍ ደረጃ ጥቃቱ አስከፊ እንደሆነ እና ለጥቃቱ አጋላጭ የሆኑ በርካታ ምክንያቶች መኖራቸው የሚታወቅ ሲሆን በዚህም የተነሳ ሴቶችና ህጻናት ለአካላዊ፣ ስነ-ልቦናዊ፣ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ጥቃት ሰላባ እየሆኑ ይገኛሉ ብለዋል፡፡

ወ/ሮ ምህረት እንደገለጹት ይህንን ጥቃት ለማስቆምም የነጭ ሪቫን ቀን መከመር መጀመሩን አውስተው በአሁኑ ሰዓትም ሀገራችን ተገዳ በገባችበት ህግ የማስከበር ተግባር ላይ በመሆኗ እና ለጦርነት ተጋላጭ በሆኑት አካባቢዎች ላይ ሴቶችና ህጻናት ጥቃት እየደረሰባቸው በመሆናቸው ይህንን መሰሉን ንቅናቄ ማድረጉ እና ሰላምን ማስፈን አስፈላጊ እና ጥቃቱን ለማስቆም እንደሚረዳ ተናግረዋል፡፡

ዳይሬክተሯ አክለውም የግቢው ማህበረሰብ እና ተማሪዎችም የጥቃቱን አስከፊነትና ችግር፣ ዘርፈ ብዙ ጉዳት በመረዳት እና ጥቃቱን ላለማድረስ ቃል ገብተው በገቡት ቃል መሰረትም ቃላቸውን እንዲጠብቁ እንዲሁም ጥቃት ደርሶም ከሆነ ጉዳት አድራሾቹ ማስተማሪያ የሚሆን እርምጃ እንዲወሰድባቸው እንዲያደርጉ እና ተጠቂዎችም የተለያዩ ድጋፎችን እንዲያገኙ ማድረግ የሁሉም ኃላፊነት መሆኑን መረዳት ይኖርበታል ብለዋል፡፡

Contact Us

Office of External Relations & Communications 
Phone:  +251 46 220 5168
International Relations
Public Relations 

Touch Us

Registrar Contact 

Registrar Directorate 
Phone: 0462200229
Email: registrar@hu.edu.et