የማህበረሰብ አግልግሎት ዳይሬክቶሬት ከሲዳማ ክልል የተለያዩ ወረዳዋች ለተወጣጡ የእንስሳት እርባታ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ስልጠና ሰጠ

የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የምርምር እና ቴክኖሎጂ ሽግግር ም/ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት ከህዳር 2-4/2014 ዓ.ም  በዩኒቨርሲቲው የአፍሪካ ህብረት አዳራሽ ለሶስት ተከታታይ ቀናት ስልጠና አካሂዷል፡፡

የማህበረሰብ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ማርቆስ ፍሰሐ ዳይሬክቶሬት መስሪያ ቤቱ በሲዳማ ክልል ለሚገኙ የቴክኖሎጂ መንደር ወረዳዎች በተለያዩ ጊዜያት በግብርና፣ አካባቢ ጥበቃ፣ ጤና እና ምግብ አጠባበቅ እንዲሁም የትምህርት ዘርፎች ላይ የተለያዩ ስልጠናዎችን እየሰጠ መቆየቱን ገልጸዋል። ይህ እየተሰጠ ያለው ስልጠናም ከእነዚህ መካከል አንዱ መሆኑን ጠቅሰው የዛሬው ስልጠና በክልሉ  ከሚገኙ  ከተለያዩ ወረዳዎች  ለተወጣጡ  ለ66 የስራ ክፍል ኃላፊዎችና ባለሙያዎች የተሰጠ መሆኑን ተናግረዋል። አክለውም ስልጠናው በዋናነት ትኩረቱን ያደረገው በእንስሳት እርባታና በእንስሳት መኖ ጥራት ማሻሻል ላይ መሆኑን እና የማህበረሰብ  አገልግሎቱ  በምርምር የተሻሻለ መኖ በማጋጀት ለአርሶ አደሩ ለማሰራጨት እቅድ እንዳለው ገልጸዋል። ሲያጠቃልሉም ሀገራችን በእንስሳት እርባታ በአፍሪካ ቀዳሚ መሆኑዋ የሚታወቅ ቢሆንም በመኖ አቀራረብና ጥራት ጉድለት ምክንያት የእንስሳት ተዋጽኦ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ያሳደረ በመሆኑ ይህን ለማሻሻል ትኩረት ተሰቶ ሊሰራ እንደሚገባ አንስተው፤ በዚህም ምክንያት ቀደም ሲል በክልላችን የቴክኖሎጂ መንደር ተብለው የሚታወቁትን 6 ወረዳዎች ወደ 11ከፍ መደረጉን አስረድተዋል።

የማህበረሰብ አግልግሎት ዳይሬክቶሬት ባለሙያ የሆኑት አቶ ጋሻው ቢኖ በበኩላቸው ስልጠናው በእንስሳት እርባታና በመኖ ጥራት ማሻሻል ዙሪያ  የሚሰጥ መሆኑን ገልጸው በቀጣይ በዶሮ እርባታና በሌሎች ስራ ዘርፎች ለተሰማሩ ማህበራት ስልጠናው የሚሰጥ መሆኑን ተናግረዋል።

በመጨረሻም የዕለቱን ስልጠና የሰጡት የዩኒቨርሲቲው መምህራንና ተመራማሪዎች የሆኑት ዶ/ር አምሳሉ ሲሳይ እና አቶ አሰፋ ታደሰ በስልጠናው የተሳተፉ የእንስሳት ባለሙያዎች ከስልጠናው የሚያገኙትን እውቀት በአግባቡ በመጠቀም በአከባቢያቸው በእንስሳት እርባታና በመኖ ጥራት ላይ የተሻለ ውጤታማነት ሊያመጡ እንደሚገባ ሐሳባቸውን ሰጥተዋል።

 

Contact Us

Office of External Relations & Communications 
Phone:  +251 46 220 5168
International Relations
Public Relations 

Touch Us

Registrar Contact 

Registrar Directorate 
Phone: 0462200229
Email: registrar@hu.edu.et