የማኑፋክቸሪንግ ምህንድስና ፋካሊቲ መምህራን የኤክስተርንሺፕ ፕሮግራም ማጠቃለያ ሪፖርት አቀረቡ

የማኑፋክቸሪንግ ምህንድስና ፋካሊቲ መምህራን የኤክስተርንሺፕ ፕሮግራም ማጠቃለያ ሪፖርት አቀረቡ።

በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት አስር የማኑፋክቸሪንግ ምህንድስና ፋካሊቲ መምህራን ጥቅምት 12 ቀን 2014 ዓ.ም ከመማር ማስተማርና ምርምር ስራዎች በተጨማሪ በሀዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ ከሚገኙ የተለያዩ ኩባንያዎች ጋር ሲያከናውኑ የነበሩትን የኤክስተርንሺፕ (ውጫዊ) ፕሮግራም ሪፖርት አቅርበዋል፡፡

ዶ/ር ተስፋዬ ባዩ በቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት የምርምርና ቴክኖሎጂ ሽግግር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር እንደገለጹት የዚህ መሰሉ ፕሮግራም ዩኒቨርሲቲውንም ሆነ ኩባንያዎቹን በጋራ የሚጠቅም በመሆኑ ኩባንያዎቹ ተግዳሮቶች ሲገጥማቸው የመፍትሄ ኃሳቦችን ለማጋኘት፣ የእውቀት ሽግግር ለማካሄድ እና የሁለትዮሽ ትስስሩን ለማጠንከር እንደ ድልድይ ሲያገለግላቸው ለዩኒቨርሲቲያችን ደግሞ የምርምር ፕሮጀክቶችን ለመቅረጽ፣ መምህራኖቻችን የማስተማር ዘዴን እንዲቀይሱ፣ ዘመኑ የደረሰበትን ቴክኖሎጂ ለተማሪዎቻቸው ለማጋራትና ተሞክሯቸውን ለማካፈል እንደሚጠቅም ገልጸው እንደሀገርም በአሁኑ ሰዓት በአምራች ኢንዱስትሪው ላይ እያጋጠሙ ያሉትን የጥራት፣ የፍጥነትና የአፈጻጸም ችግሮችን ለማወቅ፣ ለመለየትናየመፍትሔ ሀሳቦችን በማፍለቅ በዘርፉ የማማከር ስራዎችን ለመስራት ይረዳል ብለዋል፡፡

በዕለቱም መምህራኖቹ ባቀረቡት ሪፖርት ላይ የዘርፉ መምህራኖች እና ባለሙያዎች ውይይትና ግብረ መልስ ተሰጥቶባቸው ፕሮግራሙ መጠናቀቁ ታውቋል፡፡

Contact Us

Office of External Relations & Communications 
Phone:  +251 46 220 5168
International Relations
Public Relations 

Touch Us

Registrar Contact 

Registrar Directorate 
Phone: 0462200229
Email: registrar@hu.edu.et