Hawassa University (HU), Hawassa Industrial Park (HIP) Sign Memorandum of Understanding
MOU signing ceremony between HU-IOT and HIP took place at HU main campus this morning, 21 Oct. 2021. This significant step has been done for joint collaborative activities on research and development activities, objectively, to solve the current problem. According to Dr. Fasika Bete, a Scientific Director of IoT (Institute of Technology) HU transfers knowledge and professionals build experience, and graduates get recruitment opportunities in the time ahead.
Dr. Ayano Beraso, HU President, also reflected that an MOU enables both institutions to practice several activities and achieve effectively establishing the well-built and effective practicing system. Ato Fitsum Ketema, a Manager of the HIP, in his turn reflected, “We are strictly responsible to create work opportunities, to increase foreign currency, and to do in knowledge transfer next to this action solve the current problems of all levels in the country,”
ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ እና የሀዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ በጋራ በሚያሠራቸው የቴክኖሎጂ ሽግግር ጉዳዮች ላይ ስምምነት ተፈራረሙ
በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ከሀዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ ጋር ባላቸው የሙያ አግባብ በዕውቀት ሽግግር ጉዳዮች ዙሪያ ልምድ በማጎልበት ሂደት ላይ ግንኙነት ሲያደርግ ቆይቶ ለተሻለ ዓላማ ስምምነት እንዲፈረም ትልቅ ሚና ተጫውቷል፡፡ የቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ሳይንቲፊክ ዳይሬክተር ዶ/ር ፋሲካ በቴ ከኢንዱስትሪ ፓርክ ጋር በቅርበት እየሠሩ እንደነበረና በ2013 በጀት ዓመት ብቻ ከ200 የሚበልጡ ተመራቂዎች በኢንዱስትሪ ፓርኩ ሊቀጠሩ መቻላቸውን አብራርተው መምህራን ልምድ ለማግኘት ቆይታ ማግኘታቸውንና ሊያገኙ እንደሚሠራ
የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር አያኖ በራሶ በበኩላቸው ስምምነቱ ሁለቱም አካላት በተጠናከረ የአሠራር ስልት ተሳስረው ውጤታማ ተግባራትን ለማከናወን ያስችላቸዋል ብለዋል፡፡ አክለውም እንደግለሰብ ዕውቀት ለማዳበር፣ እንደተቋምም ውጤታማ ተግባትን ለመፈጸም እና እንደሀገርም ችግሮችን በማስወገድ ተጠቃሚ መሆን እንደሚቻል ተሳቢ በማድረግ ግንኙነት ማጠናከር እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል፡፡
የሀዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ ማናጀር አቶ ፍጹም ከተማ ሲናገሩ ከሥራ ዕድል ፈጠራ፣ ከውጪ ምንዛሬ ግኝት እና ከዕውቀት ሽግግር አንጻር ሀላፊነት እንደወደቀብን ከሚሰማኝ በላይ ይህን ታሳቢ በማድረግ ችግሮችን ተቀራርቦ ለመቅረፍ ወሳኝ እርምጃ በመጀመራችን እንደ ትልቅ ጉዳይ እቆጥረዋለሁ ብለዋል፡፡