የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ዓመታዊ የተመራቂ ተማሪዎች የስራ ፈጠራ ውድድር አካሄደ

የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ዓመታዊ የተመራቂ ተማሪዎች የስራ ፈጠራ ውድድር አካሄደ።

የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ከጂ.አይ.ዜድ ጋር በመተባበር በግብርና ማቀነባበሪ ዘርፍ የፈጠራ ሀሳቦችን ለማሳደግ ዩኒቨርሲቲው የተመረቁ ተማሪዎችን የስራ ፈጠራ እና ውድድር በማካሄድ የተመረጡ ሀሳቦችን በተቋሙ ቴክኖሎጂ ማበልጰጊያ ማዕከላት አስገብቶ እያሳደገ የቆየ ሲሆን በጥቅምት 6/2014ዓ.ም በአራት የስራ ፈጠራዎች መካከል የውድድርና ሽልማት ፕሮግራም በሀዋሳ ገዛኸኝና እልፍነሽ ሆቴልና ሪዞርት ተካሂዷል፡፡

ዶ/ር ባዩ ቡንኩራ የቴክኖሎጂ ሽግግር እና ኢንዱስትሪ ትስስር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር እንደተናገሩት ይህ ዓመታዊ የተማሪዎች ውድድር የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የፈጠራ ንግድ ችሎታቸውንና የስራ ፈጠራ ፍላጎታቸውን በጥልቀት በመረዳትና በመቀመር የመማሪያ ክፍል ጵንሰ-ሃሳቦቻቸውን ወደ ተግባር የሚያመጡበት ፕሮግራም ሲሆን ውጤቱም በሀገራችን ኢኮኖሚ ላይ አዎንታዊ ተጵዕኖ የሚያመጣ፣ የማህበረሰቡን ችግሮች የሚፈታ፣ ለስራ አጥ ወጣቶች የስራ ዕድል መፍጠር የሚችል እና በትምህርት ላይ ላሉ ተከታይ ተማሪዎችም አዳዲስ የቴክኖሎጂ ንግድ ፈጠራን ለማነሳሳት እንደሚረዳ ገልጰዋል፡፡

ዶ/ር ባዩ አክለውም ተወዳዳሪዎችም ከአሁን በኃላ ስራ ፈላጊዎች ሳትሆኑ ስራ ፈጣሪዎች እና ለተከታዩ ትውልድም ፈር ቀዳጆች በመሆናችሁ እንኳን ደስ አላችሁ እያልኩኝ ወደፊትም በሀገር አቀፍና በአለም አቀፍ ውድድር አሸንፋችሁ ተጥዕኖ ፈጣሪዎች እንድትሆኑ እና የዩኒቨርሲቲያችንን ስም እንድታስጠሩ ውስጣዊ ምኞቴ ነው ብለዋል፡፡

በዕለቱም በዶሮ መኖ፣ በማዳበሪያ፣ ስታርች እና የማሸጊያ አምራቾች መካከል ጋር ውድድር ተካሂዶ የስታርች አምራች ድርጅት አንደኛ በመውጣት የውድድሩ አሸናፊ ሲሆን ለተወዳዳሪዎች በጠቅላላ የዕውቅና ሰርተፍኬት እንዲሁም ከአንደኛ እስከ  ሶስተኛ ለወጡት ደግሞ ከስርተፍኬት በተጨማሪ የገንዘብ ማበረተቻ ሽልማት ተበርክቶላቸው ፕሮግራሙ ተጠናቋል፡፡

 

Contact Us

Office of External Relations & Communications 
Phone:  +251 46 220 5168
International Relations
Public Relations 

Touch Us

Registrar Contact 

Registrar Directorate 
Phone: 0462200229
Email: registrar@hu.edu.et