የትምህርት ኮሌጅ  የ2014 ዓ.ም የመጀመሪያዉ ሩብ ዓመት የእቅድ አፈፃፀም ግምገማ አካሄደ

የሀዋሳ ዮኒቨርሲቲ የትምህርት ኮሌጅ መምህራንና ሠራተኞች የ2014 ዓ.ም የሩብ ዓመት የእቅድ አፈፃፀም በገመገሙበት ወቅት ባለፈዉ ዓመት ያከናወናቸውን ስኬቶች እና የነበሩ ደካማ ጎኖች ላይ ተወያይተዋል።

በወቅቱ በነበረዉ ግምገማ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የሀዋሳ ዮኒቨርሲቲ የትምህርት ኮሌጅ ዲን ዶ/ር አብርሃም ቱሉ በ2013 ዓ.ም የተከናወኑ ተግባራትን በመጥቀስ የነበሩ ችግሮችንም አንስተዋል። በተለይ ከመማር ማስተማሩ ጋር እና ከምርምርና ከማህበረሰብ አገልግሎት ጋር በተያያዘ በኮሮና ወረርሽኝ ወቅት የግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርት እና ስልጠና መሰጠቱን ጠቁመዋል ።

ዶ/ር አብርሃም ቱሉ አክለውም በዕለቱ ለተገኙ የትምህርት ክፍሎች አስተባባሪዎች እንዲሁም ተባባሪ ዲኖች እና የአራቱ ኮሌጆች ቡድን መሪዎች ባደረጉት በ1ኛው የሩብ ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ላይ ግምገማ አድርገዋል። በዚህ ወቅትም የመፍትሄ አቅጣጫዎችን በማስቀመጥ የተሻለ አፈፃፀም ለማስመዝገብ መስራት ይኖርብናል ብለዋል።

በሀዋሳ ዮኒቨርሲቲ ትምህርት ኮሌጅ ለተከፈተዉ አዲስ የትምህርት ፕሮግራም ግብአት በሟሟላት የትምህርት ጥራትን በማሻሻል ብቁና ተወዳዳሪ ምሩቃንን ለሀገር እድገት ማዘጋጀት ይኖርብናል ሲሉ ዶ/ር አብርሃም ገልፀዋል።

Contact Us

Office of External Relations & Communications 
Phone:  +251 46 220 5168
International Relations
Public Relations 

Touch Us

Registrar Contact 

Registrar Directorate 
Phone: 0462200229
Email: registrar@hu.edu.et