በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ለሰላምና ፀጥታ ባለሙያዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ

በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ለሰላምና ፀጥታ ባለሙያዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ።

በሀዋሳ ዩኒቨርስቲ በምርምርና ቴ/ሽ/ም/ፕ/ጽ/ቤት አማካኝነት ከህግና ገቨርናንስ ኮሌጅ እና ከሲዳማ ክልል ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ጋር በመተባበር ከሲዳማ ክልል የተለያዩ ወረዳዎች ለተወጣጡ የፀጥታ ባለሙያዎች ከጥቅምት  2-3፣ 2014 ዓ.ም ለሁለት ተከታታይ ቀናት ስልጠና ተሰጥቷል፡፡ በስልጠና ወቅት በቦታው የተገኙት የዩኒቨርሲቲው ምርምርና ቴክኖሎጂ ሽግግር ምክትል ፕሬዝዳንት ዶ/ር ታፈሰ ማቲዎስ በመክፈቻ ንግግራቸው ዩኒቨርሲቲው በሀገራችን ውስጥ ከሚገኙ ስምንት የምርምር ዩኒቨርሲቲዎች መካከል አንዱ በመሆኑ የምርምር መሰረተ ልማትና ህትመቶች ተሞክሮ  በመነሳት በምግብና ስነ-ህይወት፣ በጤና፣ በሳይንስና ቴክኖሎጂ፣ ምህንድስና እንዲሁም በማህበራዊ ሳይንስ ዘርፍ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን ጠቁመው ከመንግስት የተጣለበትን ሀላፊነት ለመወጣት የአስር አመት እስትራቴጂክ እቅድ በማዘጋጀት የማህበረሰብ አገልግሎት ስራዎችን ለማከናወን ትኩረት ስቶ እየሰራ ይገኛል ብለዋል። አክለውም ዩኒቨርሲቲው በአከባቢው ካሉ ተቋማትና ኢንዱስትሪዎች ጋር ያለውን ግንኙነት ለማጠናከር እየተሰራ እንደሚገኝ ገልጸው የህግና ገቨርናንስ ኮሌጅ ትስስር ከሚፈጥራቸው ተቋማት አንዱ የሲዳማ ክልል ሰላምና ፀጥታ ቢሮ በመሆኑ በሰላም መፍጠርና በግጭት አያያዝ ላይ የድህረ ምረቃ ትምህርት እየሰጠ ያለ ከመሆኑ በተጨማሪ በዘርፉ ምርምሮችን በማካሄድና የተለያዩ አጫጭር ስልጠናዎችን በማዘጋጀት አዎንታዊ ስራ እየሰራ እንደሚገኝ አብራርተዋል። ንግግራቸውን ሲያጠቃልሉም የስልጠናው ተሳታፊዎች ሰላምና ፀጥታን ሊያደፈርሱ የሚችሉ ሁኔታዎችንና መንስኤዎቻቸውን በመለየት በሳይንሳዊ መንገድ መረጃዎችን በማሰባሰብና በመተንተን ግጭት እንዳይፈጠር ለማድረግ ከሰልጣኞቾ ብዙ ስራ እንደሚጠበቅ ገልጸዋል።

የሲዳማ ብሔራዊ ክልል ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ም/ኃላፊ አቶ ደሳለኝ በየነ በበኩላቸው መረጃ በአግባቡ መያዝና መተንተን ለሀገር ግንባታ፣ ለኢኮኖሚና ማህበራዊ ዘርፍ ስራ እንዲሁም ለፖለቲካ እንቅስቃሴ ወሳኝ እንደመሆኑ በመረጃ አያያዝና ትንተና ዙሪያ ያሉ ክፍተቶችን በጥናት በመለየት በክልላችን ከሚገኙ የተለያዩ ወረዳዎችና ከተማ አስተዳደር ለተወጣጡ 60 ለሚያህሉ ባለሙያዎች ከሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ምርምርና ቴክኖሎጂ ሽግግር ጽ/ቤት ጋር በመቀናጀት ስልጠናው መዘጋጀቱን ተናግረዋል። በመቀጠልም ክልላችን አዲስ የተዋቀረ ክልል ቢሆንም ከአጎራባች የኦሮሚያ እና ደቡብ ክልሎች ጋር በርካታ የፀጥታ ስራዎችን እየሰሩ መቆየታቸውን አውስተው፤ ሰላም ለልማትና ለመልካም አስተዳደር ግንባታ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያለው በመሆኑ የዛሬው ስልጠና ለተቀናጀ የመረጃ አሰባሰብና ግጭት አፈታት ለሚደረገው እንቅስቃሴ አይነተኛ ሚና እንደሚኖረው ጠቁመዋል።

በመጨረሻም በእለቱ ስልጠናውን ከሰጡት ባለሙያዎች መሀከል የህግና ገቨርናንስ ኮሌጅ ዲን የሆኑት ዶ/ር ደብረወርቅ ደበበ ሲናገሩ በስልጠናው የተሳተፉ የሰላምና ፀጥታ ሰራተኞች ከስልጠናው የሚያገኙአቸውን ክህሎቶች በአግባቡ በመጠቀም በግጭት አፈታቶችና ትንተናዎች ላይ የተሻለ ውጤታማነትን ሊያመጡ እንደሚገባ ሀሳባቸውን ገልጸዋል

Contact Us

Office of External Relations & Communications 
Phone:  +251 46 220 5168
International Relations
Public Relations 

Touch Us

Registrar Contact 

Registrar Directorate 
Phone: 0462200229
Email: registrar@hu.edu.et