ሀዋሳ ዩንቨርስቲ ከሌሎች አምስት የሀገራችን ዩንቨርሲቲዎች ጋር ባለፉት አራት አመታት በጤና መረጃ አብዮት ሥራ የሠራናቸውን ሥራ ለጤና ሚንስቴር ሚንስትር ዶር ሊያ ታደሰ፣ ለትምህርት ሚንስቴር ተወካዮች፣ ለዩኒቨርስቲ ፕረዚዳንቶች፣ ለጤና ሚንስቴር ዳይሬክተሮችና፣ አጋር ድርጅቶች በተገኙበት አቅርበዋል።
በስድስት ወረዳዎችና ሆስፒታሎች የተጀመረው የአቅም ግንባታና ሜንተርሽፕ ፕሮግራም አሁን ላይ አራት ወረዳዎች ሞዴል ሲሆኑ: በተለይም በሀዋሳ ዩንቨርስቲ የተገኙትን ምርጥ ተሞክሮዎችን በቀጣይ በሌሎች በተቀሩት በደቡብና በሲዳማ ክልል ወረዳዎች የማሸጋገሩ ተግባር ይሆናል።
ለዚሁ ስኬት አብራችሁን የነበራችሁ፣ በገንዘብ የደገፋችሁን በተለይም ጤና ሚንስቴር፣ DUP/DDCF ፕሮጀክት፣ እንዲሁም አብራችሁን ለሠራችሁ ለክልል ጤና ቢሮ፣ ለወረዳ ጤና ጽ/ቤቶች፣ ለጤና ጣቢያና ሆስፒታሎች ያለን አክብሮት የላቀ ነው።