ደረጃ ዶት ኮም ሀገር አቀፉን የስራ አውደ ርዕይ በሀዋሳ ለማስጀመር ዝድጅቱን ገለጸ

በአውደራዕዩ ላይ የተለያዩ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች የተገኙ ሲሆን ወጣቶችን ክፍት ስራ ቦታዎቸሀ ላይ ለማመልከትና ቀጣሪ ድርጅቶችን ለማግኘት መልካም አጋጣሚ እንደሆን የአውደራዕዩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት  የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ አስተዳዳሪና የታማሪ ጉዳይ ምክትል ፕሬዘዳንት የሆኑት ዶ/ር መሳይ ሀይሉ ተናግረዋለ፡፡

የኢንፎ ማይንድ ሶሊውሽን (ኢትዮ ጆብስ)የንግድ ሰራ ክፍል የሆነው ደረጄ ዶት ኮም ከስራ እድል ፈጠራ ኮሚሽን ጋር በመተባበር ከማስተር ካርድ ፋውንዴሽን በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ እንዲሁም ከሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ምሩቃንን ከቀጣይ ድርጅት ጋር የሚያገናኝ የስራ   አውደራዕዩ በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ በትናንትናው እለትበድምቀት ተካሂዷል ፡፡

ሲሀም አየለ የደረጃ ዶት ኮም ፕሮግራመ ዳይሬክተር እንደተናገሩት የደረጃ ዶት ኮም ከሰራ ዕድል ፈጠራኮሚሽን እና ከማስተር ካረድ ፋውንዴሽን በሚገኘው ድጋፍና  ከሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር የቀጣሪ ድርጅቶች ያስቀመጧቸውን መስፈርቶች ከበቂ በላይ በሆነ መጠን የሚያሟሉ አዲስ ተመራቂዎችን ያሳተፈዉ የ2014የስራ አዉደርዕይ ዩኒቨርሲቲዎች የሚስመረቋቸዉን ተማሪዎች በቀጥታ ከቀጣሪ ድርጅቶች ጋር እንዲገናኙ የሚያደርግ በመሆኑም ለአዲስ ምሩቃን ስራ የማግኘት ሰፊ አድል እንዲከፍት ታልሞ በደረጃ ዶት ኮም የተዘጋጀ ነዉ ብለዋል፡፡

በዚህ የስራ አዉደ ራዕይ ላይ በድምሩ እስከ 4000 ሚደርሱ ተማሪዎችና ለመቅጠር ክፍት ቦታ ያላቸዉ ከ50 በላ ቀጣሪ ድርጅቶች ተሳትፈዋል፡፡ የዚህ አይነቱ የስራ አዉደ ርዕይ መዘጋጀት ለቀጣሪ ዲርጅቶችም ሆነ ለተመራቂ ተማሪዎች ምቹ አጋጣሚ ይፈጥራል ተብሏል፡፡ ቀጣሪ ድርጅቶች ከምሩቃን ጋር በሚያደርጉት ዉይይት ከሚያሰባስቡት ካሪኩለም ቪቲ እና የትምህርት ማስረጃ ለድርጅታቸዉ ተገቢነት ያለዉን ተወዳዳሪ ሰዉ ለመለየት ከመርዳቱም በላይ በተለይ አዲስ ምሩቃን ተማሪዎች በተመረቁበት መስክ ሊኖሩ የሚችሉ የስራ እድሎችን ችንዲያዉቁና ማመልከቻ ማቅረብ ይቻላል ብለዋል፡፡

 

Contact Us

Office of External Relations & Communications 
Phone:  +251 46 220 5168
International Relations
Public Relations 

Touch Us

Registrar Contact 

Registrar Directorate 
Phone: 0462200229
Email: registrar@hu.edu.et