የተፈጥሮና ቀመር ሳይንስ ኮሌጅ በ2013 በጀት ዓመት አፈጻጸም ሪፖርትና በ2014 በጀት ዓመት ዕቅድ ላይ ምክክር አደረገ።
በግምገማና ምክክር መድረክ ላይ በመክፈቻ ንግግራቸው የተፈጥሮና ቀመር ሳይንስ ኮሌጅ ዲን የሆኑት ዶ/ር ዘይቱ ጋሻው እንደገለጹት ኮሌጁ በ2013 ዓ.ም በጀት ዓመት ከመማር ማስተማር፣ ከምርምር፣ ከማህበረሰብ አገልግሎትና የትምህርትን ጥራት ከማስጠበቅ አኳያ አዳዲስ 5 የሶስተኛና 13 የሁለተኛ ድግሪ የትምህርት ፕሮግራሞች መከፈታቸው፣ ቤተ ሙከራዎችን የማደስ፣ የማስፋትና አዲስ የማደራጀት፣ በዓሳ አመራረት ላይ የዕውቀት ሽግግር ስልጠና ከ5 ወረዳዎች ለተውጣጡ አርሶ አደሮች ስልጠና መስጠት፣ ከአረንጓዴ ልማት ጋር በተያያዘ የአካባቢ ጥበቃ፣ ከእንዱስትሪዎች ጋር ትስስሮችን የመፍጠር፣የእጅ ንጽህና መጠበቂያና ፈሳሽ ሳሙና ማምረት፣ ሀገር በቀል የዕውቀት ሽግግር ላይ ሀገር አቀፍ ውይይት ማድረግ፣ ለእንስሳት ህክምና የሚውል ሪፈራል ሆስፒታል መከፈቱን እና የዓሳ ሀብት የቤት ውስጥ ቤተ-ሙከራ መገንባቱን እና በርካታ ስራዎች መሰራታቸውን ገልጸዋል፡፡
ዶ/ር ዘይቱ አክለውም በቀጣይ የ2014ዓ.ም በጀት ዓመትም ለመድኃኒትነት የሚያገለግሉ ትክሎችን መትከያ የሚሆን ቦታዎችን (ቦታኒክ ጋርደን) ለማዘጋጀት፣ ከተክሎቹም መድኃኒቶችን በማምረት ለገበያ ለመዋል፣ ቆሻሻ አወጋገድና አስተዳደር ላይ እንዲሁም ከከርሰ ምድር ሀብትና ከመሬት መንቀጥቀጥ ጋር የተያያዙ ጥናቶችን ለማካሄድ እና ከስፖረትና መዝናኛ ጋር በተያያዘም በአካባቢው ከሚገኙ ታዳጊ ፕሮጀክቶች ጋር በጋራ ለመስራት አቅደን ለመስራት ተዘጋጅተናል በማለት ገልጸዋል፡፡
በፕሮግራሙም በቀረቡት አፈጻጸም ሪፖርትና ዕቅድ ላይ ተሳታፊዎች የተወያዩባቸውችና ቀጣይ አቅጣጫዎን ያስቀመጡ ሲሆን በዕቅድ እና ሪፖርት አዘገጃጀት ላይም ስልጠና መሰጠቱን ለማወቅ ተችሏል፡፡