በቴማቲክ ምርምር (Increasing Farming Systems Resilience to Climate Change through Climate-Smart Traditional Farming Practices)
ስር በዩኒቨርሲቲያችን ዋናዉ ጊቢ በሚገኘዉ የእርሻ ምርምር ጣብያ ላይ የተሰሩ የምርምር ስራዎች በምርምር ፕሮግራሞች ዳይሬክቶሬት፣ ተፈጥሮ እና ኮምፑቴሽናል ሳይንስ የተዉጣጡ የቢሮ ኃላፊዎች እና ተመራማሪዎች የመስክ ላይ ጉብኝት ተደርጓል። የምርምሩ ዋና ዋና ዓላማዎች እየጨመረ የመጣዉን የከባቢ አየር ሙቀት መጠን፣ የአየር ንብረት ለዉጥ ፣ የአፈር ለምነት መከላት፣ የአፈር እርጥበት እጥረት እና የመሳስሉት በግብሪናዉ ክፍለ እኮኖሚ ላይ እያደረሱት ያሉትን ተዕፅኖዎችን ለመቀነስ እና ለመቋቋም የሚያስችሉ ናቸዉ ሲሉ የምርምሩ አስተባባሪ የሆኑት ዶ/ር ጌታቸዉ ስሜ እና ሌሎች የቡድኑ አባል ተመራማሪዎች አስረድተዋል።