የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የ2013 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም እና የ2014 በጀት ዓመት መሪ ዕቅድ ላይ ውይይት በማካሄድ የግምገማ መድረኩን አጠናቀቀ

የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የ2013 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም እና የ2014 በጀት ዓመት መሪ ዕቅድ ላይ ውይይት በማካሄድ የግምገማ መድረኩን አጠናቀቀ

የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ በኢትዮጵያ የምርምር ዩኒቨርሲቲ ተብለው ከተለዩ ስምንት ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ አንዱና በ2022 ዓ.ም በምስራቅ አፍሪካ ካሉት አስር ቀዳሚ የምርምር ዩኒቨርሲቲዎች መካከል አንዱ ሆኖ ለመገኘት እየሰራ የሚገኝ ሲሆን በ2013 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም እና የ2014 በጀት ዓመት መሪ ዕቅድ ላይም በወንዶ ገነት ደንና ተፈጥሮ ሀብት ኮሌጅ ከሐምሌ15-16/2013 ዓ.ም ድረስ ውይይት አካሂዷል፡፡ የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር አያኖ በራሶ በፕሮግራሙ መክፈቻ ላይ አድርገዋል፡፡ በንግግራቸው በዚህ ዓመት በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት የተቋረጠውን ትምህርት ማስቀጠል አንደኛው ተግባር ሲሆን ይህን አጠናቅቆ የዓመቱን ሥራ ማስኬድ ከተለመደው ውጭ ጫና የነበረበት መሆኑን ጠቅሰው ከዚህ ጋር ተያይዞ የክረምት ተማሪዎችን ትምህርት ማስቀጠል ያልተቻለ ጉዳይ ሆኖ መሰንበቱን እና አሁን ግን ለመደበኛ ተማሪዎች የወጣው መርሀ ግብር እስከ ነሐሴ በመዝለቁ ይህን ተከትሎ ጥሪ መደረጉን ገልጸዋል፡፡ በሌላ በኩል በሀገር ደረጃ የተጀመረው የልማት ሥራ በአስተማማኝነት መቀጠል በሚችል መልኩ በሀገራችን የተጀመረው የግድቡ 2ኛ ዙር ሙሌት መጠናቀቁ ከመበሰሩ ጋር ተያይዞ ይህ ትልቅ ስኬትና ድል ለሁላችንም የፈጠረልን ደስታ ታላቅ በመሆኑ እንኳን ደስ አላችሁ በማለት ጉባኤውን አነቃቅተዋል፡፡ ንግግራቸውን ሲያጠቃልሉም እንደ ዩኒቨርሲቲያችንም ያለፈው ዓመት ጥሩ አፈጻጸም የታየበት ሲሆን ህብረታችን ከዚህ በላቀ ሁኔታ በሚጠነክርበት ደረጃ በቁጭት መሥራት ይጠበቅብናል ብለው መልዕክት በማስተላለፍ መድረኩን በይፋ ከፍተዋል፡፡ ሲቀጥሉም የ2013 የትምህርት ዘመን በኮሮና ወረርሽኝ በሽታ እና በተለያዩ ምክንያቶች ተደራራቢ ስራዎች የበዙበት እና ፈታኝ ወቅት መሆኑን አስታውሰው ያሉብንን ተግዳሮቶች አቅም በፈቀደ መጠን እየፈታን እዚህ የደረስን ሲሆን የ2013 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ከቀረበ በኃላ ያየናቸውን ክፍተቶች በጥልቀት በመፈተሸ በቀጣይ ዓመት እንዲስተካከሉ የመፍትሄ አቅጣጫዎችን እናስቀምጣለን ብለዋል፡፡ በፕሮግራሙ የመጀመሪያው ቀን በምክትል ፕሬዝዳንቶች ሪፖርት ቀርቦ በቀረቡት ሪፖርቶች ላይም ከተሳታፊዎች ጥያቄዎችና አስተያየቶች ተነስተው የተገባደደ ሲሆን በሁለተኛውም ቀን በተሰነዘሩት አስተያየቶች ላይ ምላሾች ተሰጥቶባቸው የ2014 በጀት ዓመት መሪ ዕቅድ በዩኒቨርሲቲው ፕላንና ተቋማዊ ለውጥ ዳይሬክቶሬት ቀርቦ ከተሳታፊዎች ጥያቄዎች ተነስተው እንዲሁም ገንቢ አስተያየቶች ከተሰጡ በኃላ ፕሮግራሙ ተጠናቋል፡፡

Contact Us

Office of External Relations & Communications 
Phone:  +251 46 220 5168
International Relations
Public Relations 

Touch Us

Registrar Contact 

Registrar Directorate 
Phone: 0462200229
Email: registrar@hu.edu.et