የ2013 ዓ.ም አዲስ ገቢ ተማሪዎች የእንኳን ደህና መጣችሁ አቀባበል ተደረገላቸው

በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የሴቶች፣ ህጻናት፣ ወጣቶችና ኤች.አይ.ቪ ኤድስ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ለ2013 ዓ.ም አዲስ ገቢ ተማሪዎች ፕሮግራም አዘጋጅቶ በዋናው ግቢ ሐምሌ1 ቀን 2013 ዓ.ም አቀባበል አድርጎላቸዋል፡፡

የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር አያኖ በራሶ በፕሮግራሙ ላይ ተገኝተው ከባለፈው ዓመት ጀምሮ ሁሉም በመጀመያሪው የትምህርት መርሃ ግብር በሚያስመዘግበው ውጤት መሰረት የሚፈልገውን የትምህርት ፕሮግራም የሚያገኝበት ዘመን በመሆኑ በርትታችሁ በመስራት ዕድላችሁን መጠቀም እንዳለባችሁ እየገለጽኩ ከቤተሰብ ተለይታችሁ እራሳችሁን የምትመዝኑበት የመጀመሪያው ምዕራፍ በመሆኑ መሰረት እንድትጥሉ ላሳስባችሁ እወዳለሁ ብለዋል፡፡

ፕሬዝዳንቱ አክለው ዩኒቨርሲቲው እናንተን ለማገልገል ሀገሪቷ ካላት ውስን ሀብት ላይ በተቻለ መጠን በመበጀት እየሰራ ሲሆን እናንተም የዩኒቨርሲቲውን ህግና ደንብ በማወቅና በመተግበር፣ ለራሳችሁም ሆነ ለቤተሰባችሁ እንዲሁም ለሀገራችሁ እንድትበቁ ወዳሰባችሁት ስኬት ለመድረስ የበኩላችሁን ጥረት ማድረግ እንደሚኖርባችሁ እየገለጽኩ እራሳችሁን ካልቆጠባችሁ ከተማችን ለመዝናናት ስለምትመች ከዓላማችሁ እንዳትሰናከሉ ልትጠነቀቁ እና ሴቶችም ለሚገጥማችሁ ችግሮች ተገቢውን ድጋፍና ምክር ከሚገባው አካል በመጠየቅና ተግባራዊ በማድረግ ለሀገርና ለትውልድ የምትጠቅሙ በመሆናችሁ እራሳችሁ ላይ ስሩበት ብለዋል፡፡

የሴቶች፣ ህጻናት፣ ወጣቶችና ኤች.አይ.ቪ ኤድስ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወ/ሮ ምህረት ገነነ  በበኩላቸው የህይወት ክህሎት ስልጠናና ተሞክሮዎችን ለተማሪዎች ያቀረቡ ሲሆን ተማሪዎችም በትምህርት ሂደት ውስጥ ችግሮች ሲገጥሟቸው ዳይሬክቶሬቱ ከምክር አንስቶ አስፈላጊውን ትብብር ለማድረግ ዝግጁ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በፕሮግራሙም ላይ በ2012 ዓ.ም ከየኮሌጆቹ  የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች የእውቅና ሽልማት ተበርክቶላቸው ፕሮግራሙ መጠናቀቁ ለማወቅ ተችሏል፡፡

Contact Us

Office of External Relations & Communications 
Phone:  +251 46 220 5168
International Relations
Public Relations 

Touch Us

Registrar Contact 

Registrar Directorate 
Phone: 0462200229
Email: registrar@hu.edu.et