የማህበራዊ ሳይንስና ስነ-ሰብ ኮሌጅ የጥራት ማረጋገጫ መሰረታውያንና ፕሮግራም ምዘና ላይ ስልጠና ሰጠ

ሰኔ 18 ቀን 2013 ዓ.ም በተደረገው የስልጠና መክፈቻ ላይ ንግግር ያደረጉት የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የአካዳሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዝዳንት ዶ/ር ፍስሃ ጌታቸው እንዳሉት እንደ ዩኒቨርሲቲ ፕሮግራሞችን ከማስፋፋትና ምርምሮችን ከማድረግ አኳያ ጠቃሚ የሆኑትን በመለየትና ጥራቶቹን በመለካት ለወደፊትም በጥራት ዙሪያ በርትተን ልንሰራ የሚገባን ጉዳይ ነው ብለዋል፡፡

ዶ/ር ፍስሃ አክለውም በሚቀጥሉት ዓመታት ፕሮግራሞችን መክፈት የምንችለው ከሀገር አቀፍ ጥራትና ምዘና ዕውቅና ሲሰጠን በመሆኑ ብቃት ያላቸውን መምህራንን በመቅጠርና በማሰልጠን ልንዘጋጅ ይገባል ብለዋል፡፡

ዶ/ር ዳኜ ሽብሩ የማህበራዊ ሳይንስና ስነ-ሰብ ኮሌጅ ዲን እንደተናገሩት ትምህርትን ከማስፋፋት አኳያ እየተሰራ ያለው ነገር ጥሩ ቢሆንም የጥራት ጉዳይ ክፍተት የሚታይበት በመሆኑ የትምህርትን ጥራት ለማስጠበቅ በርትተን ልንሰራበት ይገባል ብለዋል፡፡

በፕሮግራሙም መጨረሻ ላይ በጥራት ማረጋገጫ መሰረታዊያን፣ ዓላማ እና የትምህርት ፕሮግራሞች እንዴት እንደሚመዘኑ በምሁራኖች ቀርቦ በተሳታፊዎች ጥያቄዎችና ውይይት ተካሂዶ ፕሮግራሙ መጠናቀቁ ታውቋል፡፡

Contact Us

Office of External Relations & Communications 
Phone:  +251 46 220 5168
International Relations
Public Relations 

Touch Us

Registrar Contact 

Registrar Directorate 
Phone: 0462200229
Email: registrar@hu.edu.et