የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የህክምናና ጤና ሳይንስ ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ከሲዳማ ክልል ጤና ቢሮና ከሀዋሳ ከተማ አስ/ጤና መምሪያ ጋር በመተባበር ነበር ክንውኑን ያዘጋጀው፡፡
ዝግጅቱ የተፈጸመው ሰኔ 9 ቀን 2013 ዓ.ም ዲሆን ድንገተኛ አደጋ ተፈጥሮ ብዙ ሰዎች ሲጎዱ ታካሚዎችን ለመርዳትና ተቀናጅቶ በመስራት ህክምና ለመስጠት የሚያስተምር የተግባር ልምምድ በሀዋሳ ከተማ ቅዱስ ገብርኤል ፊት ለፊት ተከናውኗል፡፡
ዶ/ር እምነት ተስፋዬ በህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የድንገተኛና ጽኑ ህሙማን ሐኪም እንደገለጹት በተለያዩ ጊዚያቶች በሀገራችን ድንገተኛ አደጋዎች ሲደርሱ ብዙ ጊዜ ይስተዋላል፡፡ በዚህም ምክንያት የዚህን መሰል ልምምድ በሆስፒታሉ ከዚህ በፊት ያደረግን ሲሆን በዛሬው ዕለትም ድንገተኛ አደጋዎች ሲደርሱና ጉዳት የሚደርስባቸው ሰዎች ሲበዙ ተጎጂዎችን ለመርዳት የጤና ስርዓቱ ምላሽ ለመስጠት አደጋው ከደረሰበት ቦታ ጀምሮ ተገጂዎችን ከማንሳት፣ የመጀመሪያ ህክምና እርዳታ ከመስጠት፣ በአንቡላንስ ከማድረስ፣ የአንቡላንስ ስርጭት ስርዓትና እንደተጎጂዎቹ የጉዳት መጠን እንዴት የልየታ ስርዓት እንደሚከናወን እና ተቀናጅቶ ከመስራት አኳያ የተግባር ልምምድ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
በህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ በድንገተኛ ህክምና እና ጽኑ ህሙማን ረ/ፕሮፌሰር ኤፍሬም ጌጃ አንደገለጹት ድንገተኛ አደጋ ማለት በተፈጥሮም ሆነ ሰው ሰራሽ አደጋዎች ሊከሰት የሚችል የብዙ ሰው ህይወት የሚያጎድል ንብረትን የሚያወድም እንዲሁም የጤና አጠባበቅ ስርአትን የሚያዛባ እና ከተቋማት አቅም በላይ የሆነ ጉዳት ሲሆን ከዚህ የተግባር ልምምድ አደጋዎች ሲከሰቱ እንዴት ተናበን እና ተቀናጅተን መስራት እንዳለብን፣ የቱ ጋር ክፍተቶች እንዳሉብን፣ የትኞቹን የህክምና መሳሪያዎችን ማሟላት ና መጠቀም እናዳለብን እና ሁሌም ዝግጁነት ላይ ጠንክረን መስራት እንዳለብን ልምድ ቀስመንበታል ብለዋል፡፡
በተግባር ልምምዱም የህክምናና ጤና ሳይንስ ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ሀኪሞች፣ የጤና ባለሙያዎች እና የአንቡላንስ ሹፌሮች መሳተፋቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡