በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የማህበራዊ ሳይንስና ስነ-ሰብ ኮሌጅ ከምርርምርና ቴክኖሎጂ ሽግግር ም/ፕሬዚዳንት ጽ/ቤት እና ከሴቶች፣ ህጻናት፣ ወጣቶችና ኤች አይ ቪ/ኤድስ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ጋር በመተባበር በሰኔ8/2013ዓ.ም የምክክር መድረክ በዋናው ግቢ አካሄዷል፡፡
ዶ/ር አያኖ በራሶ የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ሀገራችን በአሁኑ ሰዓት የህዝብ ግፊት በወለደው የለውጥ ሂደት ውስጥ የምትገኝና በቀጣይነትም ሰላምን፣ ዲሞክራሲንና ፍትህን ለማስፈን ብዝሃነት፣ መቻቻልና ሀገር ግንባታ በጠንካራ መሰረት ላይ መገንባት ወሳኝ በመሆኑ እንዲሁም ሀገራዊ መግባባትን ማጎልበት፣ ሰላምና የመቻቻል ባህልን የመገንባት ጉዳይ ጊዜ የሚፈልግ፣ ውስብስብና በርካታ ባለድርሻ አካላትን በማሳተፍ ንቅናቄ መፍጠርን የሚጠይቅ፣ ወሳኝ ጉዳዮችን በመለየት የአጭር፣ የመካከለኛና የረጅም ጊዜ ዕቅዶችን በመንደፍ እና የላቀ የማስፈጸም ብቃትንና ክህሎትን የሚጠይቅ ከባድ ኃላፊነት ነው ብለዋል፡፡
ፕሬዚዳንቱ አክለውም እያንዳንዳችን ለግላችን፣ ለቤተሰባችንና ለአካባቢያችን ብሎም ለሀገራችን ሰላም ዘብ መቆም የሁላችን ሀላፊነት መሆኑን በመገንዘብ ሀሰተኛና ግጭት ቀስቃሽ መረጃዎችን ከማጋራት ልንቆጠብ የሚገባ ሲሆን መገናኛ ብዙሃንም የህዝብን ሰላምና ድህንንት እንዲሁም ተነጻጻሪ መብቶችና ጥቅሞችን ባከበረ መልኩ በኃላፊነት መንቀሳቀስ እንዳለባችው በመግለጽ ብዙ የቤተሰብና የማህበረተሰብ ኃላፊነቶች የተሸከሙ ሴት እህቶቻችን በዚህ ሀገራዊ ምርጫ ሚናቸው እጅግ ወሳኝ በመሆኑ የላቀ እና የተሻለ ተሳትፎ እነዲኖራቸው ያስፈልጋል ብለዋል፡፡
ዶ/ር ዳኜ ሽብሩ የማህበራዊ ሳይንስና ስነ-ሰብ ኮሌጅ ዲንእንደገለጹት የሰላምና መቻቻል ጉዳዮች እጅግ አንገብጋቢና የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጽታዎች በመሆናቸው ነጣጥለን የማናያቸው ሲሆን ሰላምና መረጋጋት ባልሰፈኑባቸው አካባቢዎች ነግዶ ማትረፍ፣ ሰርቶ መለወጥ፣ ተምሮ ለቁም ነገር መብቃት እንደማይቻልና የዜጎች ደህንነትም አጣብቂኝ ውስጥ እንደሚወድቅ ገልጸዋል፡፡
በፕሮግራሙም ላይ ዶ/ር ዮናስ አዳዬ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሰላምና ደህንነት ጥናት ዳይሬክተር እና ተባባሪ ፕ/ር አህመድ ዘካሪያ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከኢትዮጵያ ጥናት ኢንስቲትዩት ስለ ሰላም ግንባታ፣ግብዓቶች፣ ተግዳሮቹና የመፍትሄ አቅጣጫዎች ቁልፍ ንግግር ያደረጉ ሲሆን መቻቻል፣ አብሮነትና ሰላም፣ ማህበራዊ ሚዲያ እና ሴቶችና ሰድስተኛው ብሄራዊ ምርጫ በሚል ርዕስ በተለያዩ ተመራማሪዎች ጥናታዊ ጽሁፎች ቀርበ ውይይት ተደርጎባቸው ፕሮግራሙ መጠናቀቁ ታውቋል፡፡
ተ.ቁ |
የተሳታፊዎች ዝርዝር |
1 |
ደቡብ ክልል/ር/መ/ጽ/ቤትኃላፊ /ተወካይ |
2 |
ሲዳማ ክልል/ር/መ/ጽ/ቤትኃላፊ /ተወካይ |
3 |
ደቡብ ክልል ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ /ተወካይ |
4 |
ሲዳማ ክልል ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ /ተወካይ |
5 |
ደቡብ ክልል ህፃናት፣ ወጣቶችና ሴቶች ቢሮ ኃላፊ/ ተወካይ |
6 |
ሲዳማ ክልል ህፃናት፣ወጣቶችና ሴቶች ቢሮ ኃላፊ/ ተወካይ |
7 |
ሲዳማ ክልል ሰላም ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ/ተወካይ |
8 |
ደቡብ ክልል ሰላም ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ/ተወካይ |
9 |
ሲዳማ ክልል ፖሊስ ኮምሽን ኃላፊ/ተወካይ |
10 |
ደቡብ ክልል ፖሊስ ኮምሽንኃላፊ/ተወካይ |
11 |
ሲዳማ ክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊ/ተወካይ |
12 |
ደቡብ ክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊ/ተወካይ |
13 |
ሀዋሣ ከንቲባ ጽ/ቤት ከንቲባ/ተወካይ |
14 |
ሀዋሣ ከተማ አስተዳደርፖ ሊስጽ/ቤትኃላፊ/ተወካይ |
15 |
ሀዋሣ ከተማ ማህበራዊ ጉዳይጽ/ቤትኃላፊ/ተወካይ |
16 |
ሀዋሣ ከተማ ህፃናት፣ ወጣቶችና ሴቶችጽ/ቤትኃላፊ/ ተወካይ |
17 |
ሀዋሣ ከተማ ሰላም ፀጥታጽ/ቤትኃላፊ /ተወካይ |
18 |
ሀዋሣ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤትኃላፊ/ተወካይ |
19 |
ሲዳማ ክልል አቃቤ ህግ ኃላፊ/ተወካይ |
20 |
ሀዋሣ ከተማ አቃቤ ህግ ኃላፊ/ተወካይ |
21 |
ሲዳማ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮኃላፊ/ተወካይ |
22 |
ደቡብ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮኃላፊ/ተወካይ |
23 |
ሀዋሣ ከተማ ባ/ቱ/መ/ሀላፊተወካይ |
24 |
ETV ሀዋሳ ማዕከል ሀላፊ/ተወካይ |
25 |
ደቡብሬ/ቴ/ድ/ሀላደ/ተወካይ |
26 |
ሲዳማ ክልል የመ/ኮ/ጉ/ቢሮሀላፊ/ተወካይ |
27 |
ደ/ብ/ብ/ህ/ክልል የመ/ኮ/ጉ/ቢሮሀላፊ/ተወካይ |
28 |
SMN ሀላፊ/ተወካይ |
29 |
ሀዋሣ ከተማ አስተዳደር የወጣቶች ሊግ ሀላፊ/ተወካይ |
30 |
የሀገር ሽማግሌዎች (AtoEletaGabiso, and Ato Tana Butelo) |
31 |
የሀይማኖት መሪዎች(KesTekluDagole), KesisDagisewBanbura; Haji Mustefa Nasir |
32 |
የተማሪዎች ካውንስ ልሃላፊዎች( 3 from the main campus, 3 from IoT; 1 from CoA; 1from CoMHS) |