ሪፖርት ከግብርና ኮሌጅ

በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የግብርና ኮሌጅ ማህበረሰብ አገልግሎት ድጋፍ በንብ ዕርባታ ፕሮጄክት 2013 በጀት ዓመት በሸበዲኖ ወረዳ የተሰሩ ስራዎች፡-

1. ሥልጠና

ከሶስት ቀበሌ ለተመረጡ ለአስራ አምስት ንብ አናቢዎች፣ ለሶስት ልማት ሰራተኞች እና ለሁለት የወረዳ የንብ ባለሙያዎች ከሚያዝያ 25-29/2013 ዓ.ም ለአምስት ተካታታይ ቀናት በንድፈ ሀሳብ እና በተግባር የተደገፈ ስልጠና ተሰጥቷል፡፡ የስልጠናዉ ዋና ዓላማና ግብ የአርሶአደሮቹን የክህሎት ክፍተት በተግባር ስልጠና በመደገፍ እና ባህላዊ እና ኋላቀር አሰራር በዘመናዊ ተክኖሎጂ በመደገፍ የማር ምርትና ጥራት በማሻሻል ኑሮአቸዉ እንዲቀየር ማድረግ፣ በህብረት ተደራጅተዉ ምርታቸዉን ለሀገር ዉስጥ እና ለዉጪ ገበያ እንዲያቀርቡ ማስቻል፣ ስልጠና የወሰዱና ድገፍ የተደረገላቸዉ አርሶ አደሮች በቋሚነት የሀዋሳ ዩንቨርሲቲ የምርምር ቡድን እንዲሆኑ ማድረግ ነዉ፡፡

2. FTC የንብ ጋጣ ማደራጄት (Apiary site and bee shade making)

 በዚህ በጀት ዓመት የስልጠና ድጋፍ ያላገኙትን የወረዳዉን ንብ አናቢዎች በቋምነት ለማሰልጠን ማዕከል እንዲሆን አስር የንብ መንጋ መያዝ የምችል የንብ ጋጣ በFTC ተሰርቷል፡፡

3. ግብዓት መስጠት

ስልጠና ለወሰዱ አርሶ አደሮች በግል ለእያንዳዳቸዉ የተሻለ ልምድ ላላቸዉ ሁለት ዘመናዊ ቀፎ አነስተኛ ልምድ ላላቸዉ ደግሞ ሁለት የሽግግር ቀፎ፣ የንብ መከላከያ ልብስ (ቱታ፣ ዓይነርግብ፣ የእጅ ጓንት፣ ቦቲ ጫማ)፣ ማጨሻ፣ ንግስት ማገጃ፣ መሮ፣ የንብ ብሩሽ እና ዉሀ መርጫ የተሰጣቸዉ ሲሆን በቡድን ለአንድ ቀበሌ ዉድ የሆኑትን ሰም ማተሚያ፣ ማር ማጣሪያ፣ ማር መጭመቂያ እና ዓይነ በጎ ማዉጫ ተበርክቶላቸዋል፡፡

በFTC ላይ የተሰራዉን የንብ ጋጣ ለመደራጀት ደግሞ አምስት ዘመናዊ ቀፎ እና አምስት የሽግግር ቀፎ (10 ቀፎ)፣ ሰም፣ እምቤደር፣ የፍሬም ሽቦ፣ ብላዋ፣ ከተሟላ ትጥቅ ጋር ተበርክቶላቸዋል፡፡

4. የፕሮጄክቱ ዓላማና ግብ እንዲሳካ ከሸበዲኖ ወረዳ እንስሳትና ዓሳ ሀብት ቢሮ፣ ከሲዳማ ክልል እንስሳትና ዓሳ ሀብት ቢሮ እና ከሲዳማ ክልል ህብረት ሥራ ኤጄንሲ ጋር በትብብር እየሰራን እንገኛለን፡፡

Contact Us

Office of External Relations & Communications 
Phone:  +251 46 220 5168
International Relations
Public Relations 

Touch Us

Registrar Contact 

Registrar Directorate 
Phone: 0462200229
Email: registrar@hu.edu.et