የዓሳ ማስገሪያ መሣሪያዎች አሰራርና አጠቃቀም ክህሎት ላይ ለሚመለከታቸው ባለሙያዎች ስልጠና ተሰጠ

በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የአኳ-ካልቸር ምርምር እና ትምህርት ማዕከል የዓሳ ማስገሪያ መሣሪያዎች አሰራርና አጠቃቀም ክህሎት ላይ ስልጠናው እየተሰጠ ይገኛል፡፡

ለሚመለከታቸው ባለሙያዎች ከሰኔ 3 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ሰኔ12 ቀን 2013 ዓም ድረስ ለ10 ቀናት የሚቆይ  ስልጠና በዋናው ግቢ በመሰጠት ላይ መሆኑ ሲታወቅ የተፈጥሮና ኮምፕቴሽናል ሳይንስ ኮሌጅ ዲን ዶ/ር ዘይቱ ጋሻው ንግግር አድርገው ማዕከሉ ከዚህ በፊት ከባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን በደቡብ እና ሲዳማ ክልሎች በተለያዩ ወረዳዎች ለሚገኙ ባለሙያዎችና የህብረተሰብ ክፍሎች በዓሳ እና ዓሳ ሀብት ዙሪያ ስልጠናና የግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርት እየሰጠ እንዲሁም በዩኒቨርሲቲው ለምርምር፣ ሰርቶ ማሳያና የዓሳ ጫጩቶችን ለማባዛት የሚረዳ ገንዳ የገነባ መሆኑን የተባዙትን ጫጩቶችም አርሶ አደሮቹ በራሳቸው መሬት ገንዳ በማዘጋጀት እንዲያባዙ ለማህበረሰቡ በማከፍፈል  ላይ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

ዶ/ር ዘይቱ አክለውም በክልሎቹ ከሚገኙት ኃላፊዎችና አርሶ አደሮች ባደረግነው ውይይት መሰረት የዓሳ ማጥመጃ መሳሪያዎቹ በገብያው ላይ የአቅርቦት እጥረት መኖሩን በመረዳት መሳሪያዎቹን ገዝቶ ከማከፋፈል ይልቅ የዓሳ ማስገሪያ መሣሪያዎች አሰራርና አጠቃቀም እንዲሁም ሲበላሹ እንዴት መጠገን እንዳለባቸው ማሰልጠኑ ዘላቂ መፍትሄ በመሆኑ ስልጠናው የተዘጋጀ ሲሆን በዓሳና ዓሳ ሀብት ላይ መስራት የሀዋሳ ሀይቅን ጤንነት ከመጠበቅ፣ የምግብ አቅርቦትን ከማስፋት አኳያ እና በስፋት ከተሰራም የኢኮኖሚው ተጠቃሚ መሆን ስለሚቻል ጠቀሜታው የጎላ ነው ብለዋል፡፡

በስልጠናውም ላይ በዘርፉ ባለሙያዎች ስለመረብ አይነት፣ አተገባበርና አሰራር ጠቅለል ያለ ገለጻ የቀረበ ሲሆን በቀጣዮቹ ቀናትም በመረብ አሰራር እና አጠጋገን ዙሪያ የተግባር ስልጠናው እንደሚቀጥል ከማዕከሉ ባገኘነው መረጃ መሰረት ለማወቅ ተችሏል፡፡

Contact Us

Office of External Relations & Communications 
Phone:  +251 46 220 5168
International Relations
Public Relations 

Touch Us

Registrar Contact 

Registrar Directorate 
Phone: 0462200229
Email: registrar@hu.edu.et