የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ከኢትዮጵያ መምህራን ማህበር የእውቅና ሽልማት ዋንጫ ተበረከተለት

የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ላለፉት 40 ዓመታት በመማር ማስተማር፣ በምርምርና ተክኖሎጂ ሽግግር እና በማህበረሰብ አገልግሎት ላበረከተው አስተዋጾዎ ከኢትዮጵያ መምህራን ማህበር ሰኔ 2 ቀን 2013 ዓ.ም የእውቅና ሽልማት ተበርክቶለታል፡፡

ዶ/ር ዮሐንስ በንቲ የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር ፕሬዚዳንት እንደገለጹት ዩኒቨርሲቲው በኢትዮጵያ ውስጥ ካሉት አንጋፋ ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ አንዱ ሲሆን ላለፉት በርካታ ዓመታት በርካታ ምሁራኖችን በማፍራትና ለትምህርት ማህበረሰቡ እያበረከተ ያለውን አስተዋፅዖ በመገንዘብ በኢትዮጵያ መምህራን ማህበር ስም የእውቅና ሽልማት ልናበረክትላችሁ በመገኘታችን ደስታችንን እየገለጽን ሀገር መቀየር እና ለውጥ ማምጣት የምንችለው በዩኒቨርሲቲው ውስጥ ያሉ ተማሪዎችን በአግባቡ በማስተማርና በስነ-ምግባር በማነጽ በመሆኑ በርትታችሁ እንድትሰሩ አደራ እያልኩኝ ከሳይንስና ከፍተኛ ሚኒስቴር ጋርም በመተባበር አስፈላጊውን ድጋፍ እናደርጋለን ብለዋል፡፡

ኢንጅነር ቢኒያም አለማየሁ የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር በ4382 ካሬ ላይ ባለ32 ፎቅ ሁለገብ ህንጻ በአዲስ አበባ ሰንጋ ተራ አካባቢ ሊገነባ ዝግጅቱን ማጠናቀቁን እና ህንጻው ሙዚየምን፣ ባንኮችን፣ ቢሮችን እና አዳራሾችን በውስጡ የያዘ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ዶ/ር አያኖ በራሶ የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት እንደገለጹት ዩኒቨርሲቲው ላለፉት ዓመታት የሰራቸውን ስራዎች ገምግሞ ማህበሩ የእውቅና ሽልማት ስላበረከተልን እያመሰገንኩ፤ በተደረገልን ሽልማትና ማህበሩ በአዲስ አበባ ተምሳሌት የሚሆን እና በዓለም ደረጃ እይታውን ከፍ የሚያደርግ ህንጻ ሊሰራ በመሆኑ የተሰማኝንም ደስታ እየገለጽኩኝ ሽልማቱ ወደፊት ተግተን እንድንሰራ የሚያበረታታን በመሆኑ ዩኒቨርሲቲው ህንጻው ተገንብቶ እስከሚያልቅ በመደገፍ ከጎናችሁ እንደሚቆም ለማሳወቅ እወዳለሁ ብለዋል፡፡

 

Contact Us

Office of External Relations & Communications 
Phone:  +251 46 220 5168
International Relations
Public Relations 

Touch Us

Registrar Contact 

Registrar Directorate 
Phone: 0462200229
Email: registrar@hu.edu.et