የሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የማህበረሰብ ቀን በዓልን በበንሳና ዳዬ ወረዳዎች አከበረ

የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ  የሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ግንቦት 28 ቀን 2013 ዓ.ም ዕለተ ቅዳሜ የማህበረሰብ ቀን በዓል አክብሯል፡፡

በዓሉን የተከበረው ተላላፊ ባልሆኑ በሽታዎች ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርት እየተሰጠና የስኳር፣ የግፊት እና ከመጠን በላይ ውፍረት በሽታን በመመርመር ልየታ እየተደረገ ሲሆን በሲዳማ ክልል በበንሳና ዳዬ ወረዳዎች ፕሮግራሙ ተከናውኖ በርካታ የህብረተሰብ ክፍሎች ተሳትፎ አድርገዋል፡፡

በዕለቱ የተገኙት የኮሌጁ የምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ረ/ፕሮፌሰር አለሙ ጣሚሶ እንዳሉት በወረዳዎቹ  ከ20 ሺህ በላይ ነዋሪዎች የነጻ ህክምና አገልግሎት እና የግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርት ያገኙ ሲሆን በሁለቱ ወረዳዎች ለሚገኙት ማለትም ለሀቼ እና ለሀጤሳ ጤና አጠባበቅ ጣቢያ የስኳር በሽታና የደም ግፊት መመርመሪያ መሳሪያ ከኮሌጁ እንደተበረከተላቸው ገልጸው  ከችግሩ አሳሳቢነት ጋር ተያይዞ ሥራው የሚቀጥልና በወረዳዎቹም ''Grand Thematic Project'' ለመተግበር ከዩኒቨርሲቲው ተመራማሪዎችና የበላይ አመራሮች ጋር እየተጠናና እየተሰራ በመሆኑ ሲያልቅ በተቀናጀ መልኩ ለ5 ዓመት ለመተግበር ታቅዷል ብለዋል፡፡

ረ/ፕሮፌሰር ደሳለኝ ጸጋው የህብረተሰብ ጤና ባለሙያና የፕሮጀክት ማስተባበሪያ ጽ/ቤት አስተባባሪ እንደተናገሩት ቀደም ባሉት ጊዚያት ትኩረት ሳይሰጣቸው ነገር ግን አሁን በጥናት ሲፈተሸ እነዚህ ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች አሳሳቢ እየሆኑ በመምጣታቸው ለህረተሰባችን በነፃ ያሉበት ድረስ በመሄድ የግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርት፣ ምርመራ እና ልያታ እያደረግን ሲሆን ህብረተሰባችንም እነዚህ በሽታዎች ምልክታቸው በጉልህ የሚታየው ከበድ ያለ ደረጃ ላይ ሲደርሱ በመሆኑ አሳሳቢ ደረጃ ሳይደርሱ በአካባቢያቸው ባሉት የጤና ተቋማት በየጊዜው በመሄድ ሊመረመሩና በሐኪሞች የሚሰጧቸውንም ምክርና መድሃኒቶች በአግባቡ መከታተል እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡

በሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የውስጥ ደዌ ጠቅላላ ሐኪም የሆኑት ዶ/ር ዘላለም በቀለ እንደገለጹትም በሽታዎቹ ከአኗኗር ዘይቤ፣ ከምግብ አጠቃቀም፣ በቂ የሰውነት እንቅስቃሴ ካለማድረግ እና የሕክምና ክትትል ካለማድረግ እንደሚመጡ ተናግረዋል፡፡

Contact Us

Office of External Relations & Communications 
Phone:  +251 46 220 5168
International Relations
Public Relations 

Touch Us

Registrar Contact 

Registrar Directorate 
Phone: 0462200229
Email: registrar@hu.edu.et