የሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ለኮሌጁ መምህራኖችና ጤና ባለሙያዎች የአቅም ግንባታ ስልጠና ሰጠ

የሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ለኮሌጁ መምህራኖችና ጤና ባለሙያዎች የአቅም ግንባታ ስልጠና ሰጠ።

የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ለኮሌጁ መምህራኖችና ጤና ባለሙያዎች ለ5ኛ ጊዜ በዲጅታል ዳታ ኮሌክሽን (መረጃ አሰባሰብ)፣ ኳሊቴቲቭ ሪሰርች አሰራር ላይ፣ ግራንት (ድጋፍ ማግኛ)  አጻጻፍ ላይ፣ ሲስተማቲክ ሪቪው ፈንድ ሜታ አናሊሲስ ላይ በሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ከግንቦት 25-27 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ የአቅም ግንባታ ስልጠና ሰጠ፡፡

ረ/ፕሮፌሰር አለሙ ጣሚሶ የምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት  ዳይሬክተር እንደገለጹት ኮሌጁ የምርምር ኮሌጅ እንደመሆኑ የኮሌጁ መምህራን እና ባለሙያዎች በህክምናው፣በትምህርት አሰጣጥ እና በማህበረሰብ አገልግሎት ከሚሰጧቸው ግልጋሎቶች በተጨማሪ የምርምር ፕሮጀክት የመጻፍ፣የማሳደግና ድጋፎችን አፈላልጎ በማግኘት የመስራት ሙያዊ ክህሎት ሊያዳብሩ እንዲሁም በምርምር ስራዎች ላይ በሰፊው እንዲሳተፉ የአቅም ግንባታ ስልጠና እየተሰጠ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ዳይሬክተሩ አክለውም ይህ ስልጠና ሲጠናቀቅ የህብረተሰቡን ችግር የሚፈታ ምርምሮችን የሚያደርግ የተማረ የሰው ኃይል እንደሚኖር እና በቁጥርና በጥራት ደረጃ የተሻሉና የተለዩ ችግር ፈቺ ምርምሮችም ይሰራሉ  ተብሎ ይጠበቃል ብለዋል፡፡

Contact Us

Office of External Relations & Communications 
Phone:  +251 46 220 5168
International Relations
Public Relations 

Touch Us

Registrar Contact 

Registrar Directorate 
Phone: 0462200229
Email: registrar@hu.edu.et