የትምህርት ኮሌጅ ለዕጩ ሴት መምህራን የልምድ ልውውጥ እንዲያደረጉ የምክክር መድረክ አዘጋጀ

የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ትምህርት ኮሌጅ አዲስ የተቀጠሩ የኮሌጁ ሴት ዕጩ መምህራንና አንጋፋ ሴት መምህራን በህይወት ክህሎት ዙሪያ የልምድ ልውውጥ እንዲያደርጉ መድረክ አዘጋጅቷል፡፡

የ2013ዓ.ም ዕጩ ሴት መምህራን ከአንጋፋ ሴት መምህራን ልምድ እንዲካፈሉ የታሰበበት የስልጠና መድረክ ከግንቦት 24-27 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ በዋናው ግቢ አፍሪካ ህብረት አዳራሽ ተካሂዷል፡፡

ዶ/ር አብርሃም ቱሉ የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የትምህርት ኮሌጅ ዲን በመክፈቻው ላይ እንደተናገሩት ዩኒቨርሲቲው በሀገሪቱ የምርምር ዩኒቨርሲቲዎች ተብለው ከተለዩት ዩኒቨርሲቲዎች አንዱ እንዲሆን የትምህርት ኮሌጅ በመማር ማስተማር፣ በምርምር፣ በማህበረሰብ አገልግሎት እና የአቅም ግንባታ ስልጠናዎችን በመስጠት እንዲሁም የትምህርት የልህቀት ማዕከል በመሆን ጭምር በርካታ ስራዎችን እየሰራ መሆኑን ገልጸው የዚህ መድረክ አላማ  በኮሌጁ ራሳችሁን በማሳደግ በመማር ማስተማሩ፣ በምርምር እና በከፍተኛ ኃላፊነት ላይ ያላችሁ አንጋፋ ሴት መምህራን አዲስ ለተቀጠሩት ሴት ዕጩ መምህራን በህይወት ክህሎት ዙሪያ ልምዳችሁን በማካፈል ብቁ እንዲሆኑ እንድትረዷቸው ነው ብለዋል፡፡ ዶ/ር አብርሃም አክለውም ዕጩ መምህራኖች ከአንጋፋ መምህራኖቹ ጋር በግልጽ በመወያየት እና ልምድ በመውሰድ በቁርጠኝነት እና ተነሳሽነት እራሳችሁን ለማሳደግ መትጋት ሲኖርባችሁ ችግሮቻችሁን ነቅሳችሁ በመወያየትና በማውጣት ለራሳችሁ እና ለኮሌጁ ለውጥ ለማምጣት ለነገ ስንቅ የሚሆን ክህሎት እንድትጨብጡ አሳስባለሁ ብለዋል፡፡

በፕሮግራሙ ላይ ተገኝተው ስልጠና የሰጡት ወ/ሮ ምህረት ገነነ የሴቶች ህጻናት ወጣቶችና ኤች.አይ.ቪ/ኤድስ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር እንደገለጹት በየዓመቱ ለሚቀጠሩት አዲስ ዕጩ መምህራንን ለማብቃት ከኮሌጁ ጋር በጋራ እየሰራን በመሆኑ መልካም አጋጣሚና እድሉን እንድንጠቀም ያስቻለን ሲሆን ማህበረሰቡ ለጾታ በሚሰጠው ትርጉም፣ ሙያ፣ ክህሎት እነዲሁም ተደራራቢ ኃላፊነት የሴቶች ሚና ትርጉሙን አጥቷል ብለዋል፡፡ ዳይሬክተሯ አክለውም የስርዓተ ጾታ ጉዳይ በአንድ ጊዜ ለውጥ ስለማይመጣ ትኩረት ሰጥተን በወንዶች እና ሴቶች መካከል ያለውን ልዩነት ለመቅረፍ በስርዓተ ጾታ እኩልነት ላይ ተግተን መስራት ይኖርብናል ብለዋል፡፡

በፕሮግራሙም በርካታ ተያያዥ ስልጠናዎች ቀርበው እና በተሳታዎቹ ውይይት ተደርጎባቸው ስልጠናው መጠናቀቁ ታውቋል፡፡

Contact Us

Office of External Relations & Communications 
Phone:  +251 46 220 5168
International Relations
Public Relations 

Touch Us

Registrar Contact 

Registrar Directorate 
Phone: 0462200229
Email: registrar@hu.edu.et